1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የበጎ ፈቃደኛ ሀኪሞች የጌድኦ ቆይታ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2011

ጌድኦ ዞን በሚገኙ ሰባት መጠለያዎች ለአንድ ወር የሕክምና አገልግሎት የሰጡት እነዚሁ የሕክምና ባለሞያዎች በመጸዳጃ እና በውሐ እጦት ምክንያት የተፈጠሩ የጤና ችግሮችን ለመፍታት መሞከራቸውን ተናግረዋል። ችግሩ መጠነ ሰፊ መሆኑን የሚናገሩት የህክምና ባለሞያዎቹ ዘላቂው መፍትሄ ተፈናቃዮቹን ወደ የአካባቢያቸው መመለስ መሆኑንም ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/3IAsD
Äthiopien Stadtansicht Mekele
ምስል DW/M. Hailessilasie

የበጎ ፈቃድ ህክምና አገልግሎት በጌድኦ

በኦሮምያ ክልል ጉጂ አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ለተፈናቀሉ የጌዲኦ ተወላጆች የሕክምና ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩ 25 የትግራይ ክልል የሕክምና ባለሙያዎች ተልእኳቸውን አጠናቀው ተመልሰዋል። በጌድኦ ዞን በሚገኙ ሰባት መጠለያዎች ለአንድ ወር የሕክምና አገልግሎት የሰጡት እነዚሁ የሕክምና ባለሞያዎች በመጸዳጃ እና በውሐ እጦት ምክንያት የተፈጠሩ የጤና ችግሮችን ለመፍታት መሞከራቸውን ተናግረዋል። ችግሩ መጠነ ሰፊ መሆኑን የሚናገሩት የህክምና ባለሞያዎቹ ዘላቂው መፍትሄ የጸጥታ ችግሩን አስወግዶ ተፈናቃዮቹን ወደ የአካባቢያቸው መመለስ መሆኑንም ገልጸዋል። የትግራይ ክልል ከዚህ ቀደም ለጌድኦ ተፈናቃዮች የ5 ሚሊዮን ብር እርዳታ ሰጥቷል።ክልሉ የህክምና ባለሞያዎችን የጌድኦ ተፈናቃዮቹ ወደ ሚገኙበት አካባቢ በመላክ የቀጠለውን ድጋፉን  እንደሚያጠናክር  አስታውቋል። ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ ከመቀሌ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ