1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ የፖለቲካና የሲቪክ ማሕበራት ስብስብ

ዓርብ፣ ጥር 1 2012

ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣- የትግራይ ገዢ ፓርቲ ህወሓት፣ተቃዋሚዎቹ ባይቶና እና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የስብስቡ አባላት ሲሆኑ ዓረና ትግራይ፣ የትግራይ ዴሞክራስያዊ ፓርቲና ዓሲንባ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ግን አልተካተቱም

https://p.dw.com/p/3W0MJ
Gründung des Tigray Parteienverbands
ምስል DW/M. H. Brhane

የትግራይ የፖለቲካና የሲቪክ ማሕበራት መድረክ

በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ተቋማት፣ የሙያ ማሕበራትና ሌሎች ድርጅቶችን ያቀፈ «የትግራይ ፓርቲዎችና ማሕበራት ፎረም» የተሰኘ የዉይይት መድረክ ተመሰረተ፡፡ በትግራይ 'የጋራ አጀንዳዎች ' ላይ ይሰራል የተባለው መድረክ 3 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ 16 ማሕበራትን ያቀፈ ነው፡፡ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፣- የትግራይ ገዢ ፓርቲ ህወሓት፣ተቃዋሚዎቹ ባይቶና እና ሳልሳይ ወያነ ትግራይ የስብስቡ አባላት ሲሆኑ ዓረና ትግራይ፣ የትግራይ ዴሞክራስያዊ ፓርቲና ዓሲንባ ዴሞክራስያዊ ፓርቲ ግን አልተካተቱም።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ