1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢሰመኮ ላይ ያቀረቡት ተቃውሞ

እሑድ፣ መጋቢት 12 2013

ሳልሳዊ ወያነ ትግራይ፣ የታላቋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ባይቶና እና የትግራይ ነጻነት ፓርቲ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የማይካድራ የጅምላ ጭፍጨፋን አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት በተቀረው የትግራይ አካባቢ የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲፈጠር አስተዋጽዖ ነበረው ብለዋል።

https://p.dw.com/p/3quX9
Äthiopien EHRC  LOGO

የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢሰመኮ ላይ ያቀረቡት ተቃውሞ

በትግራይ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ሰብአዊ ቀውስ ገለልተኛ ሆኖ ማጣራት መቻሉ ላይ ጥርጣሬ እንዳላቸው አስታወቁ ። ሳልሳዊ ወያነ ትግራይ፣ የታላቋ ትግራይ ብሔራዊ ሸንጎ ባይቶና እና የትግራይ ነጻነት ፓርቲ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የማይካድራ የጅምላ ጭፍጨፋን አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት በተቀረው የትግራይ አካባቢ የከፋ የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲፈጠር አስተዋጽዖ ነበረው ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ በትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ ገለልተኛ የማጣራት ስራ እየሰራሁ ነው ብሏል።


ሚሊዮን ኃይለስላሴ 
ታምራት ዲንሳ