1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻርለስ ቴለር እጣ ፈንታ

ሐሙስ፣ መጋቢት 21 1998

የቀድሞዉ የላይቤሪያ ፕሬዘደንት ቻርልስ ቴይለር በስደት ተጠግተዉባት ከነበረችዉ ናይጀሪያ ለመጥፋት ሙከራ ካደጉ በኋላ ተይዘዉ በጦር ወንጀለኝነት ወደሚፈለጉባት ወደትዉልድ አገራቸዉ እንዲመለሱ ተደርጓል።

https://p.dw.com/p/E0it
ቴይለር ተይዘዉ ሞኖሮቪያ ሲገቡ
ቴይለር ተይዘዉ ሞኖሮቪያ ሲገቡምስል AP

በናይጀሪያ ፕሬዝደን ልዩ አዉሮፕላን ወደላይቤሪያ መዲና ሞኖሮቪያ የተወሰዱት ቴይለር በተባበሩት መንግስታት የሴራሊዮንን ጉዳይ የሚከታተለዉ ችሎት እንዲዳኛቸዉ ወደዚያ ሳይተላለፉ አይቀርም። በሚቀርቡበት ችሎትም በ17 የተዘረዘሩ አንቀፆች ጦርነት በመቀስቀስና የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ጨምሮ ለቀረበባቸዉ ክስ ምላሽ መስጠት ይጠበቅባቸዋል። በተጨማሪም የሴራሊዮን ፕሬዝደንት ከአዉሮፓዉያኑ 1997 እስከ 2003ዓ.ም ድረስ በአገራቸዉ በተካሄደዉ አስከፊ ጦርነት በጭካኔ ከተፈፀሙት ድርጊዎች ጋር በተያያዘ ተጠያቂ አድርገዋቸዋል።
አሁን ያለዉ አጋጣሚ ዓለም ዓቀፉ የወንጀለኞች መቅጫ ፍርድ ቤት ስራዉን በመጀመር በምዕራብ አፍሪካ ጦርነት በመቀስቀስ አስከፊ ስም ባተረፉት ቻርለስ ቴይለር ጉዳይ ብይን የሚሰጥበትን ምርመራ ማካሄድ ይችላል ተይዘዉለታልና።
በጦር ወንጀል የሚፈለጉት የቴይለር በስደት ከነበሩባት ናይጀሪያ ጠፉ የሚለዉ ዜና ግን ዓለም ዓቀፉን ህብረተሰብ አደናግሮት ነበር።
ምክንያቱም አምባገነኑ ቴይለር በላይቤሪያ 14 ዓመት ለዘለቀዉና የ400,000 የሰዎችን ህይወት ላሳጣዉ ግጭት ግንባር ቀደም ተጠያቂ ናቸዉና።
በ2004 ዓ.ም የላይቤሪያ ጦርነት ሲያከትምም የተባበሩት መንግስታት ጃኩዌስ ክላይን አስታራቂ ነበሩ።
«የቴይለር ትልቁ ሀጢያት ማህበረሰቡን ሁሉ በወንጀል ማነካካታቸዉ ነዉ፥ በህገወጥ ገበያዉ፤ በሙስናና የመንግስት ገንዘብ በማባከንና በመሳሰሉት እናም እንዲህ ያሉ ሰዎች ዋጋቸዉን ማግኘት ይገባቸዋል። ያ ካልሆነ በአፍሪካ ዉስጥ ያለዉን ይህን መሰል አመለካከት እንዴት ማስወገድና ጤናማ ህብረተሰብ መገንባት ይቻላል? የመንግስት ባለስልጣናት ሁሉ ህዝቡን በአግባቡ እንዲያገለግሉና ለህዝቡ ተጠሪ እንዲሆኑ፤ ፓሊስም በተመሳሳይ ሁኔታ ገብቶ በመንግስት ለሚካሄድ የሽብር ተግባር አስፈፃሚ ወኪል እንዳይሆን ማድረግ የሚቻልበት መንገድ እንዴት ይመጣል?»
ቴይለር አደገኛና ጨካኝ ከሚባሉት የቀድሞ አፍሪካ መሪዎች አንዱ ነበሩ።
በነሐሴ 2003ዓ.ም ከስልጣናቸዉ እንዲለቁ አግባብተዉ የናይጀሪያዉ ፕሬዝደንት ዖሊሴንጎን ዖባሳንጆ ለሁለት ዓመታት በስደት አስጠጓቸዉ።
እናም ቴይለር እስከ ተያዙባት እለት በደቡባዊ ናይጀሪያም ካላባር በተባለች ስፍራ የተቀማጠለ ቪላ ዉስጥ ነበር የከረሙት።
እኝህ ብልጣብልጥ ፖለቲከኛ የላይቤሪያን ህዝብም እጅግ አታልለዉት ነዉ በስልጣን የቆዩት ይላል በልጅነቱ ወታደር ለመሆን የተደደዉ ኬዊ ቱማ።
«በዚህ አገር አንድ መሪ ከመምረጤ በፊት በአግባቡ ማንነቱን መመርመር እንዳለብኝ ተረድቻለሁ። ምክንያቱም ባለፉት ጊዜያት ምንም ሳላዉቅ ቻርልስ ቴይለርን በመምረጤ ተሳስቻለሁ። በርካታ ወጣቶች ነበርን በየጎዳናዉ እየጨፈርን ባለማወቅ የመረትናቸዉ የተሻለ ነገር ለማየት። እናም ያለፈዉ ልለዉ የምችለዉ ለእኛ ጥሩ ትምህርት ነበር። ከአሁን በኋላ ምርጫ ሲኖር ድምፃችንን ለማን እንደምንሰጥ በአግባቡ ማወቅ ይኖርብናል።»
ዓለም ዓቀፉ ህብረተሰብ ትልቅ ስጋት የገባዉ ቻርለስ ቴይለር ወደትዉልድ አገራችዉ ላይቤሪያ እንዲመለሱ የተጀመረዉ እንቅስቃሴ ነበር።
ያም ማለት አዲሷ የላይቤሪያ ፕሬዝደንት ጆንሰን ሲርሊፍ ቴይለር ተይዘዉ እንዲሰጧቸዉ ከጠየቁ በኋላ ጉዳዩ ተንቀሳቀሰ።
ዖባሳንጆም ቢሆኑ የተደረገባቸዉ ዓለም ዓቀፍ ግፊት ቴይለርን ተገን ካገኙባት ናይጀሪያ ማስወጣት ግድ ሆነባቸዉ።
ቻርለስ ቴይለር ምናልባት ወደላይቤሪያ ለማምራት በማቀድ ሊሆን ይችላል ሾልከዉ ሲጓዙ ካሜሮን ድንበር ላይ ነዉ የተያዙት።
እኝህ የላይቤሪያ የቀድሞ አምባ ገነን መሪ ወደአገራቸዉ በደጋፊዎቻቸዉ እርዳታ እንደገና ወደስልጣን ለመመለስ አልመዉ ሳይሆን አይቀርም።
«ነገሩን ሁሉ በዚህ መንገድ የሚያይ ቡድን አለ። በላይቤሪያ ፖለቲካ ምንም ተስፋ የለንም የእኛ ብቸኛ መድህናችን ቻርለስ ጤይለር ወደስልጣን ከተመለሱ ብቻ መሆኑን እናዉቃለን የሚል አመለካከት አላቸዉ። ያ ማለት ደግሞ እኛ እየሰራን ያለዉን ዋጋ ለማስጣት በተቆጣጠሯቸዉ አካባቢዎች እንደመገናኛ ብዙሃንም ሆነ በመንግስት ስልጣን ዉስጥ ሁሉ የሚችሉትን እያደረጉ ነዉ።»
በዚህ መካከል ነዉ እንግዲህ የናይጀሪያዉ ፕሬዝደንት ዖባሳንጆ አምባገነኑን ለላይቤሪያ አሳልፈዉ የሰጧቸዉ።
ታዛቢዎች እንደገመቱትም ሴራሊዮን ዉስጥ በተባበሩት መንግስታት ልዩ የወንጀል ችሎት ለተከሰሱበት ሁሉ ምላሽ የሚሰጡበት ጊዜ አጭር ይሆናል።