1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይና እና የታንዛኒያ ግንኙነት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 26 2002

ሁለቱ ሐገራት ሾላሲታዊ ወንማማችነት ያሉትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ከአርባ-አምስት አመት በፊት ነዉ።ከአምስት አመት በሕዋላ ቻይኖች ታንዛኒያን ከአጎራባቿ ዛምቢያ ጋር የሚያገናኘዉን የባቡር መስመር ዘረጉ። ለንግባታዉ በሺሕ የሚቆጠሩ ቻይናዉያን ዘምተዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/NENU
ምስል DW

የታዛኒያዉ ፕሬዝዳት ያካያ ኪክዌቴ ባለፈዉ ዓመት ቻይናን «እዉነተኛ ወዳጅ» ብለዋታል። ፕሬዝዳንቱ በታንዛኒያ የቻይና የንግድ ተቋማት በመበራከታቸዉና የቻይና የልማት ርዳታ በመጨመሩ ደስተኛ ናቸዉ።የታንዛኒያ ሕዝብ ግን ጉዳዩን በተለየ መንገድ ነዉ-የሚያዉ።እርግጥ ነዉ የሁለቱ ሐገሮች ግንኙነት መጠናከሩን ሕዝቡ አይክድም።የዚያኑ ያክል ታንዛኒያ የሚኖሩት ቻይናዉያን ከሐገሬዉ ነዋሪ ጋር ተቀየጠዉ መኖር አይፈልጉም በማለት ቅሬታዉን ያሰማል፥ቻይኖች ሥራቸዉ ጥራት የለዉም፥በዝባዦችም ናቸዉ ባዮችም አሉ።አንድሪያን ክሪሽ የዘገበዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።
ገበያዉ።ካሪያኮ ከሚባለዉ የዳሬ ሠላም መንደር-ነዉ የሚገኝ።ከፕላስቲክ አበባ እስከ ሞተር ሳይክል፥ ከብስክሌት እስከ የአጎበር መረብ ሁሉም በሽ ነዉ።ሁሉም ሸቀጥ ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የሚገባዉ ከእስያ ነዉ።ሻጮቹም እስያዉያን ናቸዉ።ሕንዶች ታንዛኒያ ከሠፈሩ ምዕተ-አመታት አስቆጥረዋል።
አሁን ተራዉ የቻይኖች ይመስላል።ወደ አፍሪቃ እየጎረፉ ነዉ።ሐይቻንግ ዤንግ አንዱ ናቸዉ።መኪና መሸጫና መጠገኛ ድርጅት አላቸዉ።ድርጅታቸዉ ሃያ ቻይናዉያን እና አንድ መቶ አፍሪቃዉያን ሠራተኞች አሉት።ገበያዉ ጥሩ ይላሉ።
«እዚሕ የምንሠራዉ ገበያዉ ጥሩ ሥለሆነ ነዉ።የታንዛኒያ ገበያ ተጨናንቆ አያዉቅም።የሐገሬዉ ሕዝብ እዚሕ ሥንሰራ ሲያይ ደስተኛ ነዉ።የሥራ ዕድልም እንፈጥራለን።አጉርሰኝ ላጉርስሕ አይነት ነዉ።እኛን ማባረር አይፈልጉም።»
የመንግሥታቱ አቋምም እንዲያ ነዉ።ሁለቱ ሐገራት ሾላሲታዊ ወንማማችነት ያሉትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት ከአርባ-አምስት አመት በፊት ነዉ።ከአምስት አመት በሕዋላ ቻይኖች ታንዛኒያን ከአጎራባቿ ዛምቢያ ጋር የሚያገናኘዉን የባቡር መስመር ዘረጉ። ለንግባታዉ በሺሕ የሚቆጠሩ ቻይናዉያን ዘምተዉ ነበር።
የባቡር ሐዲዱ እስካሁን ድረስ ታንዛኒያ ካሏት ጠንካራ የመሠረተ-ልማት አዉታሮች አንዱ ነዉ።በላሙያዎች እንደሚገምቱት ታንዛኒያ ዉስጥ ሃያ ሺሕ ያሕል ቻይኖች ይኖራሉ።ቁጥራቸዉ እየጨመረ ነዉ።የሐገሬዉ ሕዝብ ግን የታንዛኒያ ሠራተኞች ማሕበራት ጠቅላይ ማሕበር ሊቀመንበር ወይዘሮ ማርጋሬት ማንዳጎ እንደሚሉት የቻይኖችን መበራከት በጥሩ አይን አይመለከተዉም።
«ከመንግሥት ጋር ብቻ የሁለትዮሽ ግንኙነት በነበራቸዉ ወቅት ወደ ቻይኖቹ ቀርበን አናዉቅም።አሁን ግን ብዙ ነጋዴዎች አሉ።ይሁንና ሕዝቡን እንደበፊቱ እንደራቁት ነዉ።ቻይኖች የሐገሩን ሕዝብ አይቀርቡም።የሚታዩት በየመደብሮቻቸዉ ብቻ ነዉ።ከዚያ ዉጪ አይታዩም።»

ማንዳጎ አክለዉ እንደሚሉት ቻይኖች ገንዘባቸዉን ሥራ ላይ የሚያዉሉትም እራሳቸዉን ብቻ በሚጥቀም እንጂ ለሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት በሚበጅ መስክ አይደለም።ሐገሪቱንም በርካሽ እቃ ነዉ ያጥለቀለቁት።የመብት ተማጓች ተቋማትም የቻይና የልማት ተራድዕ መርሕ የቤጂንግን መንግሥት ጥቅምና ፍላጎት ብቻ እንጂ ለሰብአዊ መብት ደንታም የለዉ በማለት በተደጋጋሚ ይወቅሳሉ።
ቻይና ብዙ ጊዜ የምትሰጠዉ ርዳታ የሚዉለዉ ለመንግሥታት ትላልቅ ፕሮጄክቶች ማስፈፀሚያ ነዉ።ሕዝቡ ከዚሕ ብዙ አይጠቀምም።በዚያ ላይ ቻይኖች ትላልቅ ተቋማትን ሲገነቡ ሠራተኞችን በሙሉ ማለት ይቻላል ከሐገራቸዉ ያስመጣሉ እንጂ የሐገሬዉን ተወላጅ አይቀጥሩም።ኬንያና ታንዛኒያ ሥለሚኖሩ ቻይኖች የሚያዉቁት ኬንያዊዉ ጆን ካሩጊያ ይሕ ሁኔታ መጥፎ ነዉ ባይ ናቸዉ።
«የአካባቢዉ ነዋሪዎችም ሥራ ሥለማግኘታቸዉ አስፈላጊነት ከበቂ ጊዜ በላይ ዉይይት ተደርጎበታል።ጉዳዩን ጠንከር አድርገዉ የሚያዩ ሰዎችም አሉ።እኔ እንደሚመስለኝ የሐገሬዉ ተወላጆች ሥራ ካገኙ ፕሮጄክቶቹንም ይበልጥ መርዳት ይችላሉ።ቻይናዉያን ብቻ የሚሠሩ ከሆነ ግን ነዋሪዉ ችግር ያመጣባቸዋል።»
ከታንዛኒያ ጎረቤት ዛምቢያ ዉስጥ ሠራተኞች ኩባንዮችን በመቃወም ባለፈዉ አመት በተከታታይ ሠልፍ ወጥተዉ ነበር።እንዲያዉም ዛምቢያ ዉስጥ ከአራት አመት በፊት በተደረገዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተወዳደሩት አንድ እጩ ከተመረጡ የቻይና ነጋዴዎችን ጠራርገዉ ለማስወጣት አቅደዉ ነበር።ያምሆኖ ቻይኖች ከነችግራቸዉ በብዙዎቹ የአፍሪቃ ሐገራት ዘንድ እንደ ጥሩ ሸሪክ እየታዩ ነዉ።

Andrian Kriesch
ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ