1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቻይና ጦር ቲቤትን የተቆጣጠረበት ሐምሳኛ አመት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 1 2001

የቻይና ኮሚንስቶች ተራራማዋን የቡደሐ-እምነት ማዕከል ቲቤትን የተቆጣጠሩበት ሐምሳኛ አመት በአል ዛሬ በመላዉ አለም በተሰደዱ የቲቤት ተወላጆች ዘንድ በተለያየ ሥርዓት እየተከበረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/H9KT
የቲቤት መንፈሳዊ መሪ ዳይላይለማምስል picture-alliance / dpa

የቻይና ጦር ቲቤቲን ሲቆጣጠር የግዛቲቱ መንፈሳዊ መሪ ዳይላይለማ ጥቂት ከጥቂት ተከታዮቻቸዉ ጋር ወደ ሕንድ የተሰደዱት ልክ የዛሬ እለት-የዛሬ ሐምሳ አመት ነበር።ሐምሳኛዉ አመት የስደት መታሰቢያ በአል በተለይ ዳይ ላይ ላማ በሚገኙበት ሕንድ ከሌላዉ አካባቢ ሁሉ በደመቀ ሁኔታ ተዘክሯል።ማቲያስ በሪንገር ያዘጋጀዉን ይልማ ሐይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል