1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኀዘን ቀን፣ ለኢጣልያ የምድር ነውጥ ሰለባዎች፣

ዓርብ፣ ሚያዝያ 2 2001

በመሃል ኢጣልያ፣ ከሮማ በስተምሥራቅ 100 ኪሎሜትር ያህል ራቅ ብላ በምትገኘው ተራራማ ከተማ ላ አኪላ፣

https://p.dw.com/p/HUcT
ኢጣልያ ውስጥ በምድር ነውጥ፣ ቁጥራቸው ከ 279 የማያንስ ሰዎች፣ ህይወታቸውን አጥተዋል።ምስል picture-alliance/ dpa

እና አካባቢው ባለፈው እሁድ ሌሊት ለሰኞ አጥቢያ በደረሰው የምድር ነውጥ የሞቱት ሰዎች ፣ ዛሬ በኢጣልያ በመላ ብሔራዊ የኀዘን ቀን በታወጀበትና ለ 2 ደቂቃ የኅሊና ጸሎት በተደረገበት ዕለት የቀብራቸው ሥነ ሥርዓት ተፈጽሟል። ሰንደቀ ዓላማዎች ዝቅ ብለው ሲውለበለቡ ውላዋል። ዛሬ ማታም የትያትርና ሲኒማ ቤቶች እንዲዘጉ ማዘጋጃ ቤት ጠይቋል። ከነገ በስቲያ፣ የጎርጎሪዮሳውያኑ የፋሲካ በዓል ከተከበረ በኋላ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ- ክርስቲያን ርእሰ-ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ ፣ የምድር ነውጥ የጎዳቸውን አካባቢዎች ይጎበኛሉ ተብሏል።

ተኽለዝጊ ገ/የሱስ፣

ተክሌ የኋላ፣

ነጋሽ መሐመድ፣

►◄