1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነአቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ቤት ዉሎ

ሰኞ፣ ጥቅምት 15 2014

በማረሚያ ቤት ውስጥ እያሉ የድብደባ ወንጀል እንደተፈፀመባቸው ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፖርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ አቤቱታቸው በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና እና በፌዴራል ወንጀል ምርመራ እንዲጣራ በፍርድ ቤት ታዘዘ።

https://p.dw.com/p/42AAE
Symbolbild Gericht Gesetz Waage und Hammer
ምስል Fotolia/Sebastian Duda

«ደብዳቢዉን ሳይሆን አስደብዳቢዉን መክሰስ እፈልጋለሁ» እስክንድር ነጋ

በማረሚያ ቤት ውስጥ እያሉ የድብደባ ወንጀል እንደተፈፀመባቸው ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፖርቲ ፕሬዝዳንት አቶ እስክንድር ነጋ አቤቱታቸው በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና እና በፌዴራል ወንጀል ምርመራ እንዲጣራ በፍርድ ቤት ታዘዘ።

Äthiopien Addis Abeba | Journalist Eskindir Nega bei Presskonferenz
ምስል DW/S. Muchie

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር እና የሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በዛሬው ዕለት ካለፈው ሳምንት ያደረውን የዐቃቤ ሕግን የ1ኛ ምስክር ድጋሜ ጥያቄ እና የፍርድ ቤት የማጣሪያ ጥያቄዎችን አድምጣል።

በመቀጠል የዐቃ ሕግ ሁለተኛ ምስክርነትን አድምጧል። ፍርድ ቤቱ ከአንደኛ ተከሳሽ ከቤተሰብ ጋር በስልክ ልገናኝ የሚልንና እና ከሁለተኛ ተከሳሽ ውጪ በግል ልታከም በሚል የቀረቡ የመብት ጥያቄዎችን ካደመጠ በኋላ ትዕዛዝ ለመስጠት ለጥቅምት 17 ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል። የዐቃቤ ሕግ ምስክር የመሥማት ሂደት ደግሞ ነገ እንዲቀጥል ችሎቱ አዟል።

ሰለሞን ሙጬ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ