1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የነዶክተር መረራ የክስ ሒደት

ዓርብ፣ ግንቦት 25 2009

ዛሬ አዲስ አበባ የተሰየመዉ ችሎት የቀድሞዉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር የዶክተር መረራ ጉዲና ጠበቃ በፅሁፍ ያቀረቡትን ቅሬታም ተቀብሎ ብይን ለመስጠት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል

https://p.dw.com/p/2e2TX
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

(Beri.AA) Dr.Merrera prozess - MP3-Stereo

                                     

የኢትዮጵያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት፤ በነ ዶክተር መረራ ጉዲና መዝገብ በተከሰሱት በኢሳት እና በኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ የተመሠረተዉ ክስ እንዲሻሻል አዘዘ።ዛሬ አዲስ አበባ የተሰየመዉ ችሎት የቀድሞዉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር የዶክተር መረራ ጉዲና ጠበቃ በፅሁፍ ያቀረቡትን ቅሬታም ተቀብሎ ብይን ለመስጠት ሌላ ቀጠሮ ሰጥቷል።ጠበቃዉ እንደሚሉት ደንበኛቸዉ በአሸባሪነት ሳይከሰሱ በአሸባሪነት የተከሰሱ የሚያስመስል መረጃ መቅረቡ ተገቢ አይደለም።የፍርድ ቤቱን ዉሎ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተከታትሎታል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ