1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኑሮ ውድነት

እሑድ፣ መጋቢት 10 2009

በቅርቡ በተለይ ለመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ማስተካከያ መደረጉ ፣ ሐገሪቱን በከፊል የመታው ድርቅ  እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የሁዳዴ ጾም መግባቱ  በመሠረታዊ ሸቀጦች  አትክልት እና ፍራፍሬዎች ላይ ለታየው የዋጋ ጭማሪ እንደ ምክንያት የሚጠቅሱ አሉ ።

https://p.dw.com/p/2ZSDF
Äthiopien Markt 2008
ምስል DW/G. Haile Giorgis

የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜያት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ እጅግ መናር ህብረተሰቡን ማማረሩ ቀጥሏል ። በቅርቡ በተለይ ለመንግሥት ሠራተኞች የደሞዝ ማስተካከያ መደረጉ ፣ ሐገሪቱን በከፊል የመታው ድርቅ  እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የሁዳዴ ጾም መግባቱ  በመሠረታዊ ሸቀጦች  አትክልት እና ፍራፍሬዎች ላይ ለታየው የዋጋ ጭማሪ እንደ ምክንያት የሚጠቅሱ አሉ ። የአቅርቦት ችግር እና ባለፈው ዓመት መጨረሻ እና በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ የተካሄደው ተቃውሞም  ለችግሩ አስተዋጽኦ አድርጓልም ይባላል ። መንግሥት በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች አካሄድኩ ባለው የዳሰሳ ጥናት በመሠረታዊ ሸቀጦች እና በአትክልት እና ፍራፍሬዎች ላይ የተደረገውን ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ምክንያታዊ አይደለም ይላል ። የኢትዮጵያ ንግድ ሚኒስቴር ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቀው ከችግሩ መንስኤዎች መካከል ሰው ሰራሽ እጥረቶች ይገኙበታል ። በዚህ አግባብ ባልሆነ መንገድ ለማትረፍ በሚሞክሩ ነጋዴዎች ላይም  እርምጃዎችን እንደሚወስድም አስታውቋል ። ይሁን እና የዋጋ ግሽበት ኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ሠሞን ብቻ የሚከሠት አይደለም ። ሥኳርን የመሳሰሉ ሸቀጦችን ጨርሶ ከገበያ እስከ መጥፋት ያደረሰው የደሞዝ ጭማሪ ከመደረጉ እና ፣ ድርቅም ሆነ ፆም ከመግባቱ በፊት ነው ።ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚያሻቅበውን የሸቀጦች ዋጋ ትርፍ ለማጋበስ የሚሹ ወገኖች የፈጠሩት ነው ማለትም ብዙዎችን የሚያሳምን ምክንያት አይደለም ። በኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት መንስኤዎች እና መፍትሄዎቹ የዛሬው እንወያያው መነጋገሪያ ርዕስ ነው ። በዚህ ላይ የሚወያዩ ሦስት እንግዶች ጋብዘናል እነርሱም፤ አቶ አዲሱ ተክሌ የኢትዮጵያ ንግድ እና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት አማካሪ ፣ አቶ ገብረ መድህን ቢረጋ የኢትዮጵያ ሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሙሼ ሰሙ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኢዴፓ የቀድሞ ዋና ፀሐፊ እና የባንክ ባለሞያ ናቸው ። የኢትዮጵያ ንግድ ሚኒስቴር ሃላፊዎች በውይይቱ ላይ እንዲሳተፉ በመስሪያ ቤቱ ህዝብ ግንኙነት በኩል ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም ።ሙሉውን ውይይት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ማድመጥ ይችላሉ ። 

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ