1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የናይጀሪያው የጎሳ ብጥብጥ

ሰኞ፣ የካቲት 29 2002

ጆሽ በተባለችው የማዕከላዊ ናይጀሪያ ከተማ ውስጥ በደረሰ የጎሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ከተገደሉ በኃላ ፀጥታ አስከባሪዎች ዛሬ በከተማይቱ በብዛት በጥበቃ ላይ ተሰማርተዋል ።

https://p.dw.com/p/MNIx
ምስል AP

የከተማዋ ነዋሪ የሆኑ የዓይን ምስክሮች እንደተናገሩት ሰዎቹ የተገደሉት ክርስቲያኖች በሚያመዝኑባቸው በጆስ አቅራቢያ በሚገኙ ሶሶት መንደሮች ውስጥ ሲሆን ጥቃቱ የተፀመውም መንደሮቹን ከበው በሚኖሩ ሙስሊሞች ነው ። ይኽው ግጭት እንደተቀሰቀሰም ሆነ ከተባበሰ በኃላ አንድም ፖሊስ በአካባቢው አለመድረሱ እያነጋገረ ነው ። የበርካታ ሰዎች ህይወት ስለጠፋበት ስለዚሁ የጎሳ ግጭት ሂሩት መለሰ የዶይቼቬለ ራድዮ የሀውሳ ቋንቋ ክፍል ባልደረባ የሆነውን ጋዜጠኛ ባላ አብዲላሂ ታኮን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች ።

ሒሩት መለስ

ነጋሽ መሐመድ