1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የናይጀሪያ እና የአሜሪካ ግንኙነት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 23 2010

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሠሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪቃ መሪዎች መካከል የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሞሐማዱ ቦሃሪን ኋይት ሐውስ ውስጥ ተቀብለው አነጋግረዋል። ንግግራቸው በዋናነት ያተኮረው በምጣኔ ሐብት እና በናይጀሪያ የጸጥታ ኹናቴ ላይ ነው።

https://p.dw.com/p/2wyAx
Kombobild Donald Trump und Muhammadu Buhari

ከሠሃራ በታች ካሉ ሃገራት ኃይት ሐውስ የተጋበዙ መሪ

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ከኾኑበት ጊዜ አንስቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ኋይት ሐውስ ቤተመንግሥት ውስጥ የአፍሪቃ መሪን ተቀብለው ፊት ለፊት አነጋግረዋል። በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት አቀባበል የተደረገላቸው የናይጀሪያው መሪ ሞሐማዱ ቦሃሪ ናቸው። ሁለቱ መሪዎች በምጣኔ ሐብት እና ናይጀሪያን በሚያመሳቅለው የጸጥታ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ «እንኳን ደስ ያላችሁ» የሚል መግለጫቸ ከሰጧቸው በአፍሪቃ የተመረጡ መሪዎች መካከል የናይጀሪያው ፕሬዚዳንት ሞሐማዱ ቦሃሪ ይገኙበታል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ