1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የናይጄሪያ ችግሮችና ብሔራዊ ጉባኤ

ረቡዕ፣ መጋቢት 10 2006

ለሰወስት ወር በሚቆየዉ ጉባኤ ከአምስት መቶ የሚበልጡ የመንግሥት፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ የሐይማኖት ተቋማት፤ የኩባንያና የንግድ ድርጅት ተጠሪዎች፤የሰራትኞች፤ የሙያና የፆታ ማሕበራት ተወካዮች፤ የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ተካፍለዋል

https://p.dw.com/p/1BRh9
ምስል SEYLLOU DIALLO/AFP/Getty Images

 

የናይጄሪያን ፖለቲካዊ፤ ሐይማኖታዊ፤ ምጣኔ ሐብታዊና ማሕበራዊ ግጭቶችንና ችግሮችን ለማስወገድ ይረዳል የተባለ ብሔራዊ ጉባኤ ዛሬ አቡጃ ዉስጥ ተጀመረ።ለሰወስት ወር በሚቆየዉ ጉባኤ ከአምስት መቶ የሚበልጡ የመንግሥት፤ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፤ የሐይማኖት ተቋማት፤ የኩባንያና የንግድ ድርጅት ተጠሪዎች፤የሰራትኞች፤ የሙያና የፆታ ማሕበራት ተወካዮች፤ የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎችና ታዋቂ ግለሰቦች ተካፍለዋል።ጉባኤዉን ያዘጋጀዉ የሐገሪቱ መንግሥት ጉባኤተኞች የአክራሪዎችና የመንግሥት ጦር ዉጊያ፤ የሐይማኖት ልዩነት ጠብ፤ የገበሬዎችና የከብት አርቢዎች ግጭት፤ የወሮ በሎች ዘረፋ፤ ሙስና እና ስራ አጥነት ግራ-ቀኝ የሚያላጋትን ሐገር ለማረጋጋት የመፍትሔ ሐሳብ ይጠቁማል ባይ ነዉ።ታዛቢዎች ግን ጉባኤዉ የተከፋፈለዉን የሐገሪቱን ገዢ ፓርቲ ከማጠናከር ባለፍ ከአፍሪቃ በሕዝብ ብዛትና በነዳጅ ዘይት የመጀመሪያዉን ሥፍራ የምትይዘዉን ሐገር የተወሳሰበ ችግር ለመፍታት የሚተክረዉ የለም።ፊሊፕ ዛንድነር የዘገበዉን የበርሊን ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል አጠናቅሮታል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ