1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኔቶ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 7 2003

በርሊን ጀርመን የተሰበሰቡት የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት ኔቶ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሊቢያ መሪ ሞአመር ጋዳፊ ኃይሎች ላይ የሚካሄደውን የአየር ድብደባ አጠናክረው ለመቀጠል ተስማምተዋል ።

https://p.dw.com/p/RIJb
ምስል picture alliance/dpa

የጦር አውሮፕላኖች እጥረት አለብኝ የሚለው ኔቶ አባል ሀገራት ለዘመቻው የሚያስፈልጉ ተጨማሪ አውሮፕላኖችን በቅርቡ ያቀርባሉ የሚል ተስፋ እንዳለው አስታውቋል ። ከመንግሥት ኃይሎች በኩል ጥቃቱ የበረታባቸው አማፅያንም የአየር ድብደባው እንዲቀጥል እየተማፀኑ ነው ። ስለ በርሊኑ የኔቶ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ የበርሊኑን ዘጋቢያችንን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሂሩት መለሰ