1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኔዘርላንድ ምርጫ ዉጤትና አንድምታዉ፤

ሐሙስ፣ መጋቢት 7 2009

ኔዘርላንድ ትናንት ባካሄደችዉ ምክር ቤታዊ ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ሩተ የቀኝ ለዘብተኛ ፓርቲ ማሸነፉ ለአዉሮጳ ኅብረትም እፎይታ መሆኑ እየተነገረ ነዉ። 17 ሚሊየን ሕዝባ ባላት ሆላንድ፤ 13 ሚሊየን ሕዝብ ድምጹን መስጠቱ ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/2ZKpK
Niderlande Premierminister Rutte PK Uni Rotterdam
ምስል Getty Images/AFP/E. Dunand

Beri Brüssel (Netherlands election result 2017) - MP3-Stereo

በዚህም ሙስሊም ጠል የሆኑትና የሕዝብ ድጋፍ አላቸዉ የሚል ስጋት አሳድረዉ የነበሩትን ኸሪት ዊልደርስን በድምጹ መቅጣት መቻሉ ተገልጿል። የምርጫ ዉጤቱ ለባለ ድሉ እና ፓርቲያቸዉ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤት ሃገራትም የደስታ ምንጭ መሆኑ ታይቷል። እንዲያም ሆኖ መንግሥት ለመመሥረት የሚያስፈልገዉ አብላጫ ድምጽ ባለማግኘቱ የጥምር መንግሥት እንደሚመሠርት ይጠበቃል። ከብራስልስ ገበያዉ ንጉሤ ዉጤቱ እና አንድምታዉን አስመልክቶ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ