1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የተቃዉሞ እንቅስቃሴ እና እንድምታዉ  

ዓርብ፣ ጥቅምት 4 2009

በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለዉ ሕዝባዊ ተቃዉሞ የንብረት ዉድመትና ጥፋት ማስከተሉ፤ መሠረታዊዉን የመብት ጥያቄ እያደበዘዘዉ ነዉ ሲሉ ነዋሬዎች ገለፁ። የፖለቲካ ተንታኞች በበኩላቸዉ የንብረት ዉድመቱ የሕዝቡን የመብት ጥያቄ ቢያደበዝዘዉም ትግሉን ግን ሊገታ አይችልም ሲሉ አስተያየት ይሰጣሉ። 

https://p.dw.com/p/2RFgC
Proteste in Äthiopien
ምስል Reuters/T. Negeri

Ethio protest and violence - MP3-Stereo

 


በኢትዮጵያ ለወራት የዘለቀዉ የፀረ መንግሥት የተቃዉሞ እንቅስቃሴ የሰዉ ሕይወት እያጠፋና ንብረት እያወደመ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ መብትና ነጻነት የሚጠይቁትን ጭምር እያሳሰበ የመጣ ይመስላል።  ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉ አስተያየት ሰጭ እንደሚሉት ከሆነ ፀረ መንግሥት ተቃዉሞ ከሰላማዊነቱ አንፃር አብዛኛዉ ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘ ነበር። ይሁንና በተወሰኑ አካባቢዎች የደረሰዉ የንብረት ዉድመትና  ማነትና ያነጣጠረዉ ጥቃት ዋናዉን የመብትና የነጻነት ጥያቄ እንዳያጠለሸዉ ያሳስባል ብለዋል። ሌላዉ አስተያየት ሰጭ በበኩላቸዉ ተቃዉሞ ወደ ንብረት ዉድመት የሄደበት ምክንያት የሕዝቡ ጥያቄ በአግባቡ ሰሚ ባለማግኘቱ ነዉ ይላሉ። አስተያየት ሰጭዉ አክለዉም በእንዲህ አይነቱ የተቃዉሞ እንቅንቅስቃሴ ላይ ከመብት ጥያቄ ዉጪ ሌላ አላማ ያላቸዉ ሊኖሩ እንደሚችሉ ገልፀዉ እነዚህን ሕዝቡ በንቃት ሊጠብቅ እንደሚገባ ተናግረውል። የፖለቲካ ተንታኙ  አቶ የሱፍ ያሲን በበኩላቸዉ በሕዝቦች ትግል እንዲህ ዓይነት ነገሮች የተለመደ መሆኑን ገልፀዉ፤ የሕዝቡን የመብት ጥያቄ ለጊዜዉ ሊሸፍን እንጂ፤ ሊያቆመዉ እንደማይችል ይገልፀዋል።  


ፀሐይ ጫኔ

ነጋሽ መሐመድ