1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኖርማንዲ ዘመቻ መታሰቢያ

ሐሙስ፣ ግንቦት 29 2011

የተባባሪዎቹ ሐገራት ወታደሮች፣ ከአዉሮፕላን እየወረዱ ፈረንሳይን ይቆጣጠሩ ከነበሩ የጀርመን ጠላቶቻቸዉ ጋር የገጠሙት ዉጊያ ብዙ ሺሕ  ሠራዊት ያለቀበት፣ የቆሰለና የተማረከበት ግን የጦርነቱን የኃይል ሚዛን የቀየረ ዉጊያ ነበር።

https://p.dw.com/p/3JzE9
Friedhof Normandy American Cemetery
ምስል DW/C. Martens

በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወቅት የናትሴ ጀርመንን ለመዉጋት ያበሩት ሐገራት ጦር ኖርማንዲ ባሕር ዳርቻ፣ ፈረንሳይ ያረፈበት 75ኛ ዓመት ተከብሮ ዋለ።በበዓሉ ላይ በጦርነቱ የተሳተፉ ሐገራት መሪዎች፣ በሕይወት የሚኖሩ የቀድሞ ወታደሮችና የተለያዩ ሐገራት መልዕክተኞች ተካፋዮች ነበሩ።እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ሰኔ 6፣ 1944 የተባባሪዎቹ ሐገራት ወታደሮች፣ ከአዉሮፕላን እየወረዱ ፈረንሳይን ይቆጣጠሩ ከነበሩ የጀርመን ጠላቶቻቸዉ ጋር የገጠሙት ዉጊያ ብዙ ሺሕ  ሠራዊት ያለቀበት፣ የቆሰለና የተማረከበት ግን የጦርነቱን የኃይል ሚዛን የቀየረ ዉጊያ ነበር።D-DAY ተብሎ የሚጠራዉ ዕለት የጀርመንን ሽንፈት፣ የተባባሪዎቹ ሐገራትን ድል ያመለከተ፣ አዲሲቱን አዉሮጳን የቀረፀ ተብሎም ይጠራል።ዕለቱን ምክንያት በማድረግ የፓሪሷ ወኪላችን ኃይማኖት ጥሩነሕን በስልክ አነጋግሪያታለሁ።

Frankreich 75. Jahrestag D-Day Normandie - Macron und Trump
ምስል Reuters/C. Barria

ኃይማኖት ጥሩነሕ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ