1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኖርዌይ ዓለም አቀፍ የእርዳታ ሚንስትርና ኢትዮጵያ፧

ዓርብ፣ ነሐሴ 25 1999

የኢትዮጵያ መንግሥት ስድስት የኖርዌይ ዲፕሎማቶች አገር ለቀው እንዲወጡለት ከሰሞኑ መወሰኑ የሚታወስ ነው። ምንድን ነው የተፈጠረው ችግር?

https://p.dw.com/p/E0XE
ምስል Peter Zimmermann
ኖርዌይ ምን ትላለች፧ ዓለም አቀፍ የልማት ሚንስትሯን ኤሪክ ሶልሃይምን ዛሬ ስልክ በመደወል አነጋግሬአቸው ነበር።
«የኢትዮጵያ መንግሥት ጥቂት ያቀረባቸው ክሶች ኖርዌይ መጥፎ ባህርይም ሆነ ምግባር አሳይታለች ነው፧ ክሱ በጥቅሉ! ይህን ክስ እኛ አንቀበለውም። ይሁንና ኖርዌይ፧ እንዲህ ዓይነት ው’ዝግብ እንዲፈጠር ከቶውንም ፍላጎቷ አይደለም። እንደምናምነው፧ ኢትዮጵያ ከታወቁት የአፍሪቃ አጎች አንዷ ናት። የአፍሪቃ ኅብረት መቀመጫ ናት በህዝብ ብዛት ረገድም ዐቢይ ግምት የሚሰጣት ናት። እናም፧ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር፧ ግንኙነቱ እንደገና እንዲሠምር የተቻለውን ጥረት እናደርጋለን።«
የኖርዌይ መንግሥት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ውህግብ ያለበቸውን ፓርቲዎች በመሸምገል ሰላም እንዲፈጠር ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ መቆየቱ ነው የሚነገርለት፧ እንደምሳሌ የእሥራኤልንና የፍልስጤምን የሲሪላንክንና የታሚል ታይገውስ አማፂ ኃይልንና የመሳሰሉትን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል። በአፍሪቃው ቀንድ የኖርዌይ መንግሥት ለየት ያለ እርምጃ ወስዷል ማለት ነው?!
«በአፍሪቃው ቀንድ አካባቢ ያደረግነው፧ ኖርዌይ በሌሎች የዓለም መድረኮች ከምታከናውነው ጋር አንዳች ልዩነት የለውም። የተግባራችን መመሪያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ደንቦች ናቸው። ከውዝግብ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በቀጥታ ከሚመለከታቸው ጋር እንነጋገራለን። በማንኛውም ዓይነት ውዝግብ ላይ ላሉ ሰላም በ,ኣት ረገድ ጠቃሚ ድርሻ ለማበርከት ከመጣርና ሰላም እንዲፈጥሩ ከመርዳት የተለዬ የምናራምደው ጥቅም-አዘል ጉዳይ የለንም«።
The Norway Post የተባለው ድረ-ገጽ ሆነ ጋዜጣ፧ አሁን ከኢትዮጵያ ጋር የተፈጠረውን የግንኙነት መሻከር፧ በልማት እርዳታ አቅርቦቱ ላይ ተጽእኖ ሊኖረው እንደሚችልም ሆነ የእርዳታው መርኡእብር ሊቀነስ እንደሚችል በዓምዱ ላይ አሥፍሯል። ኖርዌይ፧ በያመቱ ለኢትዮጵያ ከ 40-50 ሚልዮን ዶላር የሚገመት የልማት እርዳታ እንምታቀርብ ቢገለጥም በዲፕሎማቶች መቀነስ፧ የልማት ፕሮጀክቶችን በብቃት መምራት ስለሚያዳግት 5 ሚልዮን ዶላር ይቀመሣል ተብሏል።
« የኢትዮጵያ መንግሥት አዲስ አበባ የሚገኘው ኤምባሲያችን ዲፕሎማቶች ቁጥር ከ ዘጠኝ ወደ ስድስት ዝቅ እንዲል ወስኗል። ሦስት ዲፕሎማሶች ብቻ የልማት ፕሮጀክቶችንም ጭምር በመከታተል፧ ለመሥራት እንደማይቻላቸው ማንም የሚገነዘበው ይመስለኛል። እኛ የተለያዩት ፕሮጀክቶች ሁሉ ደረጃቸውን ጠብቀው በብቃት እንዲከነወኑ ነው የምንፈልገው። ስለዚህ ሦስት ዲፕሎማቶች መምራት ይሳናቸዋል። በዚህ ተጨባጭነት ባለው ምክንያት ሳቢያ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ፕሮጀክቶቻችንን አንዳንዶቹን መቀነስ ግድ ይሆንብናል። ያም ሆኖ በኖርዌይና ኢትዮጵያ፧ በሁለቱ አገሮች መካከል ዲፕሎማሲያዊው ግንኙነት እንከን ቢያጋጥመውም፧ የሲቭሎች፧ የመንግሥት ያልሆኑ ድርጅቶች፧ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተግባራት ያላንዳች ሳንክ እንደሚቀጥሉ እናምናለን።«
የረጅም ጊዜ ማለፊያ ግንኙነት ያላቸው አገች በመሃሉ የተበላሸ የመሰለው ግንኙነት እንዲስተካከል የሚያደርጉበት ዕድልም ሆነ እንቅሥቃሴ ካለ እንዲያብራሩልን የኖርዌዩን የዓለም አቀፍ የልማት ሚንስትር Erik Solheim ን መጨረሻ ላይ ጠይቄአቸው ነበር።
«እኛ ከኖርዌይ መንግሥት በኩል፧ የኢትዮጵያ መንግሥት የወሰደውን ውሳኔ አንቀበለውም። በሌላ በኩል ይህ ክርክርም ሆነ ንትርክ እንዲቀጥል አንፈልግም። ስለዚህም ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የግንኙነትን መሥመር ተጠቅመን ይህን ጉዳይ እንዴት ልንፈታው እንደምንችል እንነጋገራለን። የዲፕሎማቲክ ጥረታችንን እንገፋበታለን። ከሁለቱ አገሮች ሚንስትሮች ተገናኝተው ይመክሩበታል የሚል ግምትም አለኝ። እናም ከዚህ ያልሠመረ የዲፕሎማሲ ይዞታ መውጣት የሚቻልበትን መላ ለመፈለግ ጥረት እናደርጋለን።«