1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኖቤል የሰላም ሽልማት ና ቻይና

ሐሙስ፣ ኅዳር 30 2003

በነገው ዕለት ኦስሎ ኖርዌይ ውስጥ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓት ይካሄዳል ።

https://p.dw.com/p/QUR3
የኖቤል የሰላም ተሸላሚ ሉዊ ዥያቦምስል AP

ይሁንና የዘንድሮው ተሸላሚ ቻይናዊው ሉዊ ዥያቦ በእስር ላይ ስለሆኑ በስነ ስርዓት ላይ መገኘት አይችሉም ። በነገው ስነ ስርዓት ላይ ለሉዊ ዥያቦ የተያዘው መቀመጫ ብቻ ሳይሆን የተወሰኑ ወንበሮችም ባዶ መሆናቸው አይቀርም ። ከቻይና ጋር ሌሎች ሀያ ሀገራትም በሽልማቱ አሰጣጥ ላይ አይገኙም ። እነርሱም ሩስያ ዩክሬይን ሰርብያ ካዛክስታን ኮሎምብያ ቬንዝዌላ ኩባ ቱኒዝያ ሞሮኮ ግብፅ ሱዳን ሳውዲ አረቢያ ኢራቅ ኢራን አፍጋኒስታን ፓኪስታን ሲሪላንካ ቬይታንም እና ፊሊፒንስ ናቸው ። ምክንያታቸው ምን ይሆን ?

ማትያስ ፎን ሀይን

ሂሩት መለሰ

ነጋሸ ሞሀመድ