1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሌፖ ጥቃት እና ያስከተለው ውግዘት

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 20 2008

ድንበር የማይገድበው የሀኪሞች ድርጅት፣ «ሜድሰ ሶን ፍሮንትየር» በሶርያ የአሌፖ ከተማ በአንድ ሀኪም ቤት ላይ ትናንት ሌሊት የተጣለውን አስከፊ ጥቃት በሶርያ የድርጅቱ ኃላፊ ሙስኪልዳ ዛንካዳ በጥብቅ አወገዙ።

https://p.dw.com/p/1IetR
Syrien Krieg Kämpfe in Aleppo
ምስል Getty Images/AFP/A. Alhalbi

በአል ቁድስ ሀኪም ቤት ላይ በተጣለው ጥቃት ከተገደሉት ቢያንስ 14 ሰዎች መካከል ሁለት የሀኪሞቹ ድርጅት ዶክተሮችም እንደሚገኙባቸው ዛንካንዳ አክለው አመልክተዋል። እጎአ ከ2012 ዓም ወዲህ በአል ቁድስ የሚሰራው ድንበር የማይገድበው የሀኪሞቹ ድርጅት 34 አልጋዎች ፣ ስምንት ዶክተሮች እና 28 ነርሶች አሉት። ያካባቢ ነፍስ አድን ሰራተኞች እንደሚሉት ግን፣ በአል ቁድስ ጥቃት የሟቾች ቁጥር እስከ 30 ይደርሳል፣ ብዙዎች ፣ ሕፃናትም ጭምር ቆስለዋል። ተቃዋሚዎች ጥቃቱን የሶርያን መንግሥት የሚደግፈው የሩስያ አየር ኃይል እንደጣለው ነው ያመለከቱት። ጥቃቱ ከተለያዩ አቅጣጫዎችም ውግዘት አፈራርቋል። ተቀናቃኞቹ የሶርያ ተፋላሚ ወገኖች የተኩስ አቁም ደንብ ከደረሱ ከሁለት ወር በኋላም በሀገሪቱ የቀጠለው ውጊያ በሁለቱ መካከል በዠኔቭ የተጀመረው የሰላም ድርድር ላይ ጥላ አጥሎበታል። ድርድሩን የሚመሩት የተመድ ልዩ የሶርያ ልዑክ ስታፈን ደ ሚስቱራ የተኩስ አቁሙ ደንብ ጨርሶ እንዳይፈርስ በማስጠንቀቅ፣ ዩኤስ አሜሪካ እና ሩስያ የሶርያን የርስበርስ ጦርነት በማብቃቱ አኳያ ባስቸኳይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲያነቃቁ አሳስበዋል።
« የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ኦባማ እና የሩስያ አቻቸው ፑቲን ከዚህ ቀደም የወሰዱት እና ጥሩ ውጤት ያሳየው ርምጃ ፍፃሜውም ያማረ እንዲሆን የሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ አመራሮች ተጨማሪ ርምጃ እንዲወስዱ እማፀናለሁ።

Syrien Friedensverhandlungen in Genf Staffan de Mistura
ምስል Reuters/D. Balibouse

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ