1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአልበሺር የአስመራ ጉብኝትና የኣፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ

ዓርብ፣ ጥር 9 2006

የሱዳኑ ፕሬዝደንት ኦመር ሓሰን አልበሺር፣ ለሶሳት ቀናት ጉብኝት ትላንት አስመራ መግባታቸው ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/1Asgj
Omar al-Bashir Archivbild 2012
ምስል picture alliance/abaca

የጉብኝቱ ዓላማ በሁለቱ ኣጎራባች መንግስታት መካከል ያለውን ኣገራዊ ግኑኝነት ከማጎልበት ባሻገገር፣ ተንታኞች እንደሚያመለክቱት፣ በደቡብ ሱዳን ከተቀጣጠለው ቀውስ ጋር በተያያዘ ሰሜን ሱዳን ኣጋጣሚውን ተጠቅማ ፍላጎቷን ለማሳካት የጀመረችው ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ አካል ነው ተብሏል።

በኖርዌይ ስታቫንገር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶ/ር ግሩም ዘለቀ እንደሚሉት የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ንግግርን ጨምሮ የኣልበሺር ተልዕኮ ኡጋንዳ በደቡብ ሱዳን የጀመረችውን ወታደራዊ ጣልቃገብነትንም የሚመለከት ሊሆን ይችላል።

ዶ/ር ግሩም ዘለቀ ኤደራ የተባለ ዓለም ዓቀፍ ተቐም ኣማካሪም ናቸውr፣ ያነጋገራቸው ጃፈር ዓሊ ነው።

ጃፈር ዓሊ

ነጋሽ መሓመድ