1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ አሳሳቢ ይዞታ

ረቡዕ፣ የካቲት 13 2011

በአማራ ክልል የሚገኘው አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ይዞታው አሳሳቢ መሆኑ እየተነገረ ነው። የፓርኩ ችግር ሌሎች ደኖቻቸው እየተጨፈጨፉ በመራቆት፣ ወይም በሌላ ምክንያት ለአደጋ የተጋለጡ ፓርኮች አይነት አይደለም።  

https://p.dw.com/p/3DfIv
Äthiopien Amhara Nationalpark
ምስል DW/A. Mekonnen

ትኩረት የሚፈልገው የአልጣሽ ፓርክ

አብዛኛው ሜዳማ መሆኑ የሚነገርለት አልጣሽ ፓርክ በጎረቤት ሱዳን ከሚገኘው ዲንደር ፓርክ ጋር የሚጎራበት ነው።  የአካባቢው ነዋሪ በተለምዶ ፈላታ የሚላቸው ከቦታ ቦታ በመዘዋወር እንደሚኖሩ የሚነገርላቸው የናይጀሪያ ከብት አርቢ ፉላኒዎች ፓርኩን መኖሪያቸው ማድረጋቸውን ነው፤ ዋናው ችግር።  እንደተጠቀሰውም ፓርኩ ውስጥ የሚገኙት የናይጀሪያ ፉላኒ ጎዳ ሰዎች 10 ሺህ ይገመታሉ። የእንስሳቱም ቁጥር ከመቶ ሺህ በላይ እንደሚሆን ተገልጿል። ሰዎቹ ድንበር ከመነሻቸው ናይጀሪያ ተጉዘው ድንበር ጥሰው በተጠቀሰው አካባቢ መከማቸታቸው ፓርኩን ለአደጋ እያጋለጠው እንደሆነ ነው የተነገረው። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ !

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ