1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሐዱ ራዲዮ ጋዜጠኞችና የፖሊስ ምርመራ

ረቡዕ፣ ግንቦት 21 2011

የጣቢያዉ ኃላፊ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ እንደሚለዉ እራሱን ጨምሮ አራቱ ጋዜጠኞች ለመጪዉ ሳምንት ሐሙስ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተስጥቷቸዋል።

https://p.dw.com/p/3JSbk
Äthiopien Eröffnung Ahadu Radio
ምስል DW/Y. G. Egziabhare

የአሐዱ ጋዜጠኞችና የፖሊስ ምርመራ

የአሐዱ ራዲዮ ጣቢያ ኃላፊን ጨምሮ የጣቢያዉ አራት ባልደረቦች ሰንዳፋ ፖሊስ ጣቢያ ቃላቸዉን ሰጥተዉ ፍርድ ቤት ለመቅረብ በዋስ መለቀቃቸዉን አስታወቁ።የጣቢያዉ ኃላፊ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ እንደሚለዉ እራሱን ጨምሮ አራቱ ጋዜጠኞች ለመጪዉ ሳምንት ሐሙስ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተስጥቷቸዋል።አንድ የአሐዱ ራዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኛና ሌላ ባልደረባዉ «የተዛባ ዘገባ» አሰራጭታችኋል በሚል ፖሊስ ባለፈዉ አርብ አስሮ ሰኞ ነበር የፈታቸዉ።ጋዜጠኛ ጥበቡ እንደሚለዉ የፖሊስ ርምጃ የጋዜጠኞችን የመዘገብ ነፃነት የሚጋፋ ነዉ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ