1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራና የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ቅርርብ፤ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ

ዓርብ፣ መስከረም 2 2012

በቅድምያ «DW» ዎች ዶቼዎች፤ ዶቼ ቬለዎች እያላችሁ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መግለጫ ላስተላለፋችሁልን ተከታታዮቻችን ሁሉ እናመሰግናለን። እኛም መልካም አዲስ ዓመት ጤና ሰላምና ፍቅርን እንመኛለን! እንኳን ከዘመን ዘመን አሸጋገራችሁ! የተወደዳችሁ የ «DW» ዶቼ ቬለ ቤተሰቦች!  

https://p.dw.com/p/3PZQD
Flyer Äthiopisches Neujahrfest 2012
ምስል DW/A. Hahn

የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝት

ሰሞኑን የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ተከታታዮች በርካታ አስተያየቶች ከተሰጡባቸዉ ርዕሶች መካከል የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መግለጫ እና የኑሮ ዉድነት፤ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስሀን ጥሩነህ የአዲስ ዓመት ምኞት መግለጫን አስታከዉ በአዲሱ ዓመት በክልላቸዉ እና በትግራይ ክልል ፖለቲከኞች መካከል ያለዉን ቅሪታ በጠረቤዛ ዙርያ መፍትሄ ለመስጠት ዝግጉጁ መሆናቸዉን መናገራቸዉን  በተመለከተ እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን ምዕመናን በሃገር ዉስጥ እና በተለዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ምዕመናን በቤተ-ክርስትያኒቱ የሚደርሰዉን ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም ለመጠየቅ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራታቸዉ የተሰኙ ርዕሶች ይገኙበታል።
«በቅድምያ «DW» ዎች ዶቼዎች፤ ዶቼ ቬለዎች እያላችሁ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መግለጫ ላስተላለፋችሁልን ተከታታዮቻችን ሁሉ እናመሰግናለን። እኛም መልካም አዲስ ዓመት ጤና ሰላምና ፍቅርን እንመኛለን!» «ጋሻዉ አድማሱ የተባሉ አድማቻችን ፤ በአዲሱ ዓመት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚ/ር ወደ ዋጋ ግሽበት ሚ/ር ፤ በሌላ በኩል የትምህርት ሚ/ር  ወደ ብስባሽ ሚ/ር ቢቀየር ይሻላል! መልካም አዲስ ዓመት ብለዋል።» «አልሚ ዋጋ በበኩላቸዉ በዓሉ በዓል አይመስልም ፤ የኑሮ ዉድነቱ እጅግ በጣም ጨምሮአል ብለዋል።» «ሚኒሊክ ዳግማዊ በበኩላቸዉ ለሁላችሁም የ «dw» አዘጋጆች እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ። አዲሱ ዓመት ለአገራችንና ለህዝቦቿ ሁሉ የሰላምና የጤና የመፈቃቀርና የመተሳሰብ ብሎም ዘረኞች የሚጠፉበትና ያለልዩነት የነበረን የኢትዮጲያዊነት እሴቶች የሚመለሱበት ሰላም የምናገኝበት ዓመት ያድርግልን! ሲሉ በምስጋና አስተያየታቸዉን  ቋጭተዋል።»  
«በቃ እኔ ምንም ሳልገዛ በተለመደው መልኩ የእለት ከእለት ኑሮየን በመኖር በዓሉን ለማሳለፍ ወስኛለው፤ ኑሮው ከበደኛ! ያሉን ደግሞ ላስታዉስሽ ታከለ ፈቃደ ናቸዉ።» «ቴዲ ኢትዮጵያ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ፤ የኩራት ቀን ሲከበር አምስት መቶ ብር የበዓል ዶሮ ዋጋን እያሰብኩ  ቆዝሜ ዋልኩ ሲሉ ነዉ አስተያየታቸዉን ያስቀመጡት።» «አንድነት ታደሰ ደግሞ ይጠይቃሉ ፤  እኛ እኮ በዓመት ሦስት ጊዜ ብቻ ነው የምንጠግበው። እሱም የዘመን መለወጫ፤ የገና እንዲሁም የፋሲካ ዕለት ነው ያለው ማን ነዉ? መልስ አስቀምጠዋል፤ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር» «እያዩው አማረ ተበጀ ደግሞ ፤ በዓሉን አስበነው እንውላለን። ከሽንኩርት አቅም 30 ብር በገባበት ጊዜ በፌስታ ማሳለፍ ዘበት ነው። ይህም ይሁን አሁን የናፈቀን ሀገራችን ሰላም እምትሆንበት ጊዜ ነው። እናንተን እናመሰግናለን።» በቅርቡ ጥቁር መነጥር መፋቅያ ካፖርታ መግዛታቸዉን ጠቆም ያደረጉን የፊስቡክ ተከታታይ አሸናፊ በትረ ያስቀመጡት አስተያየት፤ ፈገግ ያሰኛል። ደሞ የምን አዲስ ዓመት ያሉም ይመስላል እንዲህ አሉ በጥያቄ «የኩራት ቀን ካከበርኩ አይበቃኝም ? በኩራት ቀን ምክንያት ዋጋ የጨመሩ እቃዎች፡~ ጥቁር መነፅር ፡ ካፖርታ ፡ መፋቅያ፡ የእጅ ሰዓት ፡ ወዘተ ሲሆን ህብረተሰቡ በዋጋ ግሽበቱ ተማሯል።» «ሌላዉ የፊስ ቡክ ተከታታይ በበኩላቸዉ የኩራት ቀን በያመቱ ጳጉሜ 4 ቢከበር ኮርቶ ለማያቁ የኔቢጤ አይነቶች በዓመት ብያንስ አንዴ ለመኩራት ጥሩ አጋጣሚ ይፈጥራል» 
አቃቂ/ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ሆነዉ አስተያየታቸዉን በፌስ ቡክ ያደረሱን ውሽንፍር ውሽንፍር የተባሉ ተከታታይ፤ በመጀመሪያ ሁላችንንም በሰላም ላደረሰን አምላክ ምስጋና ይድረሰዉ እያልኩ፤ እኔ ባለሁበት አቃቂ/ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ዉስጥ ያሉ ነጋዴዎች ዋጋ ለመጨመር ተማክረዉ የዛኑ ቀን ማታ ገበያዉ በእሳት ቃጠሎ ወድሟል። የሚገርመዉ ዛሬ 1 ኪሎ ሽንኩርት 17 ብር መሸጡ ገርሞናል! ይሄ ነገር እዉነት ይሁን ሀሰት እስቲ አጣሩ?» ብለዋል ። ከአቃቂ መልስ የሚሰጠን እንደምናገኝ ተስፋ አለን። 
«DW ዎች እንኳን አብሮ አደረሠን! ሲሉ መልስ ያስቀመጡልን ተዘራ መኩርያ ምን ዋጋ አለው ፤ ድሮ ሽንኩርት ሲልጡት ነበር እሚያስለቅሠው፤ አሁን አሁን ሲገዙት ማስለቀስ ጀምሯል» ብለዋል። «የበግ ዋጋ በጣም ከመወደዱ የተነሳ የበግ ቅርጫ ውስጥ ለመግባት ተገደናል፤ ያሉት ደግሞ ተስፋዬ ፋንታሁን ናቸዉ። » «አዋሽ ገዳሙ የተባሉ የ«DW» ተከታታይ በበኩላቸዉ፤ ሁሉም አዲሱ ዓመት የሰላም እንዲሆን ይመኛል! ጥሩ ነው! ግን የተንኮል የምቀኝነት የማሰመስል ውሸቶች ለስልጣን ሲባል በውሸት የማጣላት ፖለቲካ ካልቆመ ሰላም በምኞት ይመጣል ተብሎ አይታሰብም» ብለዋል። 
«በኑሮ ዉድነት ዓመት በአሉን ለማስቀረት የታሰበ ነዉ የሚመስለዉ። የኑሮ ዉድነቱ በዚህ የሚቀጥል ከሆነ እጅግ አሳሳቢ ነዉ! ያዉም በእኛ ሀገር፤ ኑሮ ከእጅ ወደ አፍ በሆነበት። አንድ መዘንጋት የሌለበት ነገር አገሪቷን እየመራት ያለዉ ነጋዴ ነዉ ባይ ነኝ! ለምን ቢባል? የሸቀጥ ዋጋ ጨመረ ነዉ እንጅ ቀነሰ የለም!» ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) እና የአማራ ዴሞክራሲዊ ፓርቲ (አዴፓ) ቅራኔን በተመለከተ “በአዲሱ ዓመት ችግሮቻችን በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀመጠን ተወያይተንና ተግባብተን ለመፍታት ዝግጁ ነን” ከ(ሕወሓት) ወገንም ተመሳሳይ ፍላጎት ይኖራል ብለን እናምናለን ሲሉ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞት መግለጫቸዉን አስታከዉ፤ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተናገሩትን አስመልክቶ ፤  መኳንንት ዝናዉ « ዋው በጣም ደስ የሚል ዜና ነው መልካም አዲስ ዓመት እንዲሆን እመኛለሁ በተለይ የአማራነትህን ጥያቄ በአዲሱ ዘመን ይህን መልዕክት ስላስተላለፈው በጣም ደስ ብሎኛል በተለይ ለትግራይ ህዝብ እንዲሁም ለአማራ የፍቅር የሰላም የብልጽግና የአብሮነት ዘመን እትዲሆን እመኛለሁ መልካም አዲስ ዓመት ይሁንልን ።» ብለዋል።  
«ታሪኩ ደሳለኝ የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት ሁሌም አለ። ሁሉ ቦታ ይታያል! ዘላቂ መፍትሄው፡ በአስተሳሰብ ከሚመስልህ ጋር አብረህ መጓዝ ነው። ከማይመስልህ ጋር በጊዜ መለያየት» ብለዋል። «ዳዕሮና ሻፋ የተባሉ አድማጭ ፤ ኢትዮጵያ እድል ፈንታዋ በሶስቱ ወጠምሻ ብሔሮች እጅ ነው ያለው እነዚህ ወጠምሻ ብሔሮች ከተስማሙ እንኳን የኢትዮጵያ ሰላም የአፍጋኒስታ ሰላምንም መጠበቅ ይችላሉ። እነዚህ ሦስት ጉዙፍ ብሔሮች አነስ አነስ ያሉ ብሔሮችን በሰላም እንዳይኖሩ እነሱ በተቧቀሱ፤ በተናከሱ፤ በተራገጡ ቁጥር አናሳዎቹ እየተጎዱ ነው። ስለሆነም ከሦሶስት ሺህ ዓመታት በላይ አብሮ የኖረ የተዋለደ ዕድሩ ዕቁቡ አንድ የሆነ ሕዝብ ምን አረገ? ኢትዮጵያ ሰፊ ነች የተፈጥሮ ሐብቷ እንኳን ለኢትዮጵያውያን ለአፍሪካውያን ይበቃል። ሁሉም ክልሎች ሐብታም ናቸው። ስለሆነም ሰላማችን ይመለስልን። እኑኑርበት! ቁማር አትጫወቱብን። ይሄ ሕዝብ ለሦስት ቀን የምትሆን ጥራጥሬ የሌለው ነው። የሚበዛው ሕፃናት፤ ሕመምተኛ፤ ሽማግሌ፤ ይሄ ሁሉ ሰላም ይፈልጋል። ብአዴን እና ሕወሐት እንሆ እልሕ ተያይዛችሁ ይህው ጦሱ ለሌላው ተረፈ ወይ ተፋቱ ወይ ተፋቀሩ»

Temesgen Tiruneh Äthiopien Regionalregierung
ምስል DW/A. Mekonnen

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ- ክርስትያን ተቋማት የጠሩትን የሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በአዉሮጳና ሰሜን አሜሪካ መስከረም አራት ተመሳሳይ ሰልፍ ሊያካሂዱ መሆኑ ተሰምቶአል። ባለፈዉ ማክሰኞ አዲስ አበባ ላይ በተሰጠዉ መግለጫ ሰላማዊ ሰልፉ በቤተ-ክርስትያኒቱ የሚደርሰዉን ግፍና ሰቆቃ እንዲቆም ለመጠየቅ ነዉ! ተብሎአል። ይህንኑ በተመለከተ በርካታ የ«DW»ተከታታዮች አስተያየቶችን ሰጥተዋል።  ጃራ ብሩ የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ «እዚህ አገር የሰልፍ ፋሽን አልፏል። አሁን የሚጠራው ሰልፍ የሚጠቅም አይደለም። ችግር ቢኖር እራሱ ቀጭብሎ መወያየቱ ይጠቅማል። የዉሽት ሰልፍ አትጥሩ።  ትርፉ ጩኸት ነዉ። ሆያ ሆዬ ብቻ ነዉ» ብለዋል። 
«የእምዬ ተዋህዶ ከኢትዮጵያ አልፎ ከአድማስ አድማስ ይመለከተኛል እሚል ዕልፍ አዕላፋት ተቆርቋሪ ያላትን እሚፃረር ፅንፈኛ ከራሱ ጋር የተጣላ ጋኔል ነውና እግዚአብሔር ይገስፀው» ሲሉ አስተያየታቸዉን የወረወሩት ደግሞ እስክያልፍ ያለፋል የተባሉ የፌስቡክ ተከታታይ ናቸዉ። ሳባፍ አማርዲን ቡንጃ ፤ የተባሉ ደግሞ ሰላማዊ ሰልፉ የኦሮምያን ቤተክህነት መቃወም ካልሆነ ታድያ ለመደገፍ ነዉ በአሁኑ ወቅት ሰላማዊ ሰልፍ ያስፈለገው? » ሲሉ ጠይቀዋል። «ሰልፍንኳን ይቅርባችሁ። ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብሳል። ነገ ጧት ደሞ እናንተን እሚቃወም ሰው ሰልፍ ልውጣ፣ ትግስት ጥሩ ነው፤ ታገሱ።  ከኛ ከሙስሊሞችም ተማሩ እኛ ብዙ አሳልፈናል»  ሲሉ የፃፉት የፊስቡክ ተከታታይ አሚና ወሎየዋ ይባባላሉ»  
እኔ ይኼ የሃይማኖት ጉዳይ በጣም እያሳሰበኝ ነው። ሲሉ አስተያየታቸዉን የጀመሩት አብርሃም ይሳቅ ናቸዉ። ሃይማኖትን ለፖለቲካ ጉዳይ ማስፈጸሚያ ማድረግ ብዙ ችግር የሚያመጣ ነው። ምናልባት እንዲህ የሚያስቡ ሰዎች  ሊፈጠር የሚችለው ነገር ምንም ግድ ያልሰጣቸውና የማያስጨንቃቸው ናቸው። በተለይ በህገወጥ መንገድ እየተንቀሳቀሱ ላለው ለቄስ በላይ የሚያደርጉት ነገር ሊያመጣ የሚችለውን ነገር አልገባቸውም። እነሱ የሚለኩሱት እሳት ሊፈጃቸው እንደሚችል ያወቁ አይመስለኝም።» 
«ሁምናሳ ጌላና በበኩላቸዉ ይህቺ ቤተ-ከርስቲያን መቼ ነው ከፖለቲካ ፍቺ የሚትፈፅመው? ከምንሊክ እስከ ኃይለሥላሴ ከመንግሥት ጋር ጋብቻ መሥርታ ከመንግሥት ጋር ሆና ህዝባችንን ስትጨቁን ቆየች። እንዲህ ስል እምነቱ ችግር አለበት ማለት ሳይሆን በቤተ- ክርስቲያን ውስጥ የተሸሸጉ ፖለቲከኞች ቤተ-ከርስቲያኒቱን ምሽጋቸው አድርገው የፖለቲካ ፎላጎታቸውን ሲያከናወኑ ቆዩ፤ ዛሬ ያን ለመመለስ ቀን ተሌት እየሰሩ ነው። ላይሳካላቸው! ብለዋል። »  «ዋናው የኦሮሚያ የቤተ-ክህነትን ጥያቄ በይፋ መቃወሙ አሳፋሪ መሆኑን መረዳታቸው ነው። ግን እነሱ አንቃወምም ቢሉም ለምን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ ግልፅ ነው "ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ" ይላል አማራ ሲሉ የፈገግታ ምልክትን ያስቀመጡት አስተያየት ሰጭ ማሪፍ አብደላ ይባላሉ። ያም ሆነ ይህ ሀይማኖታዊ ጉዳይን ውይይት እንጂ ሰልፍ አይፈታውም ሲሉ አስተያየታቸዉን የፃፉት ተማም ሁሴይን ናቸዉ።

Bahru Tefera,
ምስል DW/Y. Gebregziabher

አዜብ ታደሰ 
እሸቴ ተክሌ