1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ መስተዳድርና የባሕርዳር ፀጥታ

እሑድ፣ ሰኔ 16 2011

በመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራና በግድያዉ ማግስት ዛሬ የባሕርዳርም ሆነ አዲስ አበባ ከተሞች ፀጥታ የተረጋጋ መሆኑን የየአካባቢዉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።የአማራ ክልል ምክትል ርዕሠ መስተዳድር እንዳስታወቁት የባሕርዳር ፀጥታን የክልሉና የፌደራል ፀጥታ አስከባሪዎች በቅንጅት እየጠበቁ ነዉ

https://p.dw.com/p/3KxhT
Äthiopien Brigadegeneral Asamnew Tsige
ምስል DW/A. Mekonnen

የአማራ መስተዳድርና የባሕርዳር ፀጥታ

 

በመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራና በግድያዉ ማግስት ዛሬ የባሕርዳርም ሆነ አዲስ አበባ ከተሞች ፀጥታ የተረጋጋ መሆኑን የየአካባቢዉ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።የአማራ ክልል ምክትል ርዕሠ መስተዳድር እንዳስታወቁት የባሕርዳር ፀጥታን የክልሉና የፌደራል ፀጥታ አስከባሪዎች በቅንጅት እየጠበቁ ነዉ።በመፈንቅለ መንግሥቱ ሙከራ የተገደሉትን የአማራ ርዕሠ መስተዳድር ዶክተር አምባቸዉ መላኩን ተክተዉ የክልሉ ምክትል ርዕሠ መስተዳድር አቶ ላቀዉ አያሌዉ እየሰሩ ነዉ።የባሕርዳሩ ወኪላችን አለምነዉ መኮንን እንደዘገበዉ ባሕርዳር ኢንተርኔት የለም፣መረጃ የሚሰጥ አካል የለም፣የመንግስትም ሆኑ የተቃዋሚ ፖለቲከኞች የስልክ ጥሪ አይመልሱም።

አለምነዉ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ