1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ

ረቡዕ፣ የካቲት 27 2011

አንድ የምክር ቤት አባል ለDW እንደተናገሩት ጉባኤው እየተወያየባቸው ካሉ ጉዳዮች መካከል ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን ውዝግብ መፍታት የሚቻልበት መንገድ ይገኝበታል። ትናንት ደግሞ የምክር ቤቱ አባላት በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ የሰላም እጦት ላይ ባተኮረ ጽሑፍ ላይ በቡድን ተወያይተዋል።

https://p.dw.com/p/3EYoZ
Äthiopien Amhara Ratssitzung in Bahir Dar
ምስል DW/A. Mekonnen

የአማራ ክልል ምክር ቤት 12 ተኛ መደበኛ ጉባኤ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 12 ተኛ መደበኛ ጉባኤ በምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ንግግር  ዛሬ በይፋ ተጀምሯል። ምክር ቤቱ በዚህ ጉባኤ በክልሉ ሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በዝግ እየተወያየ መሆኑ ተነግሯል። አንድ የምክር ቤት አባል ለDW እንደተናገሩት ጉባኤው እየተወያየባቸው ካሉ ጉዳዮች መካከል ከአጎራባች ክልሎች ጋር ያለውን ውዝግብ መፍታት የሚቻልበት መንገድ ይገኝበታል። ትናንት ደግሞ የምክር ቤቱ አባላት በአንዳንድ አካባቢዎች በተፈጠረ የሰላም እጦት ላይ ባተኮረ ጽሑፍ ላይ በቡድን መወያየታቸውን የባሕር ዳሩ ወኪላችን ዓለምነው መኮንን ዘግቧል። 
ዓለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ