1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአማሮ ልዩ ወረዳ የተቃዋሚ ፓርቲና የመንግሥት ዉዝግብ

ዓርብ፣ የካቲት 19 2002

በደቡብ ኢትዮጵያ በአማሮ ልዩ ወረዳ የሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ የአድነትና የዲሞክራሲ መድረክ አባላትና ደጋፊዎች የመንግሥት ባለሥልጣናት ያስሩናል፥ ያንገላቱናል በማለት ወቀሱ።

https://p.dw.com/p/MDKl
ምስል AP GraphicsBank/DW
በልዩ ወረዳዉ የፓርቲዉ ተወካይ እንደሚሉት የወረዳዉ አስተዳዳሪዎች የፓርቲዉን ፅሕፈት ቤቶች ይዘጋሉ፥አባል ደጋፊዎቻቸዉን ያስራሉ፥ ያንገላታሉም።የልዩ ወረዳዉ ባለሥልጣናት ግን ወቀሳዉን አጣጥለዉ ነቅፈዉታል።የልዩ ወረዳዉ አስተዳዳሪ ከዚሕም አልፈዉ መስተዳድራቸዉ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር የዉይይት መድረክ አዘጋጅቶ ችግሮችን ለማስወገድ እየጣረ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ ሁለቱንም ወገኖች በስልክ አነጋግሮ ያጠናቀረዉ ዘገባ አለ። በልማዱ-መድረክ በሚል አጭር ስም የሚጠራዉ የኢትዮጵያ የአድነትና የዲሞክራሲያዊ መድረክ ፓርቲ የአማሮ ልዩ ወረዳ ተጠሪ አቶ አማረ ገብረ ሚካኤል የመንግሥት ሹማምንታት ያደርሱብናል የሚሏቸዉ በደሎች ብዙና ከባድ ናቸዉ። የልዩ ወረዳዉ አስተዳዳሪ አቶ ሞገስ ሞርማ እንደሚሉት ግን መስተዳድራቸዉ ያደረሰዉ በደል።ተቃዋሚዎችም ፅሕፈት ቤት ከፍተዉ በነፃነት እየተንቀሳቀሱ ነዉ-የላሉ የተቃዋሚዉ ፓርቲ ተወካይ አቶ አማረ ገብረ ሚካኤል አሁንም የታሰሩ አሉ ባይ ናቸዉ። የልዩ ወረዳዉን አስተዳዳሪ አቶ ሞገስ ሞርማን ጠየቅኋቸዉ።መለሱም። የተቃዋሚዉ ፓርቲ ተወካይ አቶ አማራ ገብረ ሚካኤል የመንግሥት አካላት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎችን ከማሰር፥ ከማንገላታት፥ፅሕፈት ቤትን ከመዝጋት አልፈዉ የርዳታ እሕል እንኳን እየነፈጉን ነዉ-ይላሉ። የልዩ ወረዳዉ አስተዳዳሪ አቶ ሞገስ ሞርማ በዚሕ አንወቀስም ባይ ናቸዉ። ሁለቱ ወገኖች የሚወቃቀሱባቸዉን ጉዳዮች ለምፋትም ሆነ የየበላዮቻቸዉ መፍትሔ እንዲሰጡበት ለማድረግ ያቀዱት ሥለመኖር-አለመኖሩ እስካሁን ያሉት ነገር የለም። ነጋሽ መሀመድ ሂሩት መለሰ