1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን ምክር ቤት እና የ CIA ውዝግብ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 8 2001

የአሜሪካን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ዲክ ቼኒ እና በአሜሪካን የስለላ ድርጅት CIA ላይ ምርመራ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ነው ።

https://p.dw.com/p/IpYc
ዲክ ቼኒምስል AP

CIA የአልቄይዳ መሪዎችን ለመግደል የሚሰማሩ ቡድኖችን ለማቋቋም ያቀደውን አሁን ግን የተቋረጠውን ምስጢራዊ መርሀ ግብር ማሳወቅ ሲገባው በዲክ ቼኒ ቀጥተኛ ትዕዛዝ መደበቁ ከፍተኛ የህግ ጥሰት መሆኑ ተጠቁሟል ። በሌላ በኩል የፍትህ ሚኒስቴር የቀድሞውን የአሜሪካን ፕሬዝዳንት የጆርጅ ቡሽን አስተዳደር የቁም ስቅልና የእንግልት መርሀ ግብር ለክስ ሊያቀርብ እንደሚችልም እየተነገረ ነው ። ዝርዝሩን አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ፣ሸዋዬ ለገሠ