1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን ተጨማሪ እርዳታ

ዓርብ፣ ነሐሴ 6 2003

አሜሪካን በረሃብ ለተጠቃው የአፍሪቃ ቀንድ ተጨማሪ እርዳታ ለመስጠት መወሰኗን አስታወቀች ።

https://p.dw.com/p/RfmH
ምስል AP

የአሜሪካን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን ትናንት በሰጡት መግለጫ ሃገራቸው በድርቅና ረሃብ ለተጎዱት የአፍሪቃ ቀንድ አገራት የ 17 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ እርዳታ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል ። ከዚህ እርዳታ ከሁለት ሶስተኛ በላይ የሚሆነውንም ለሶማሊያ የሚለገስ ነው ። ክሊንተን በዚሁ መግለጫቸው ተመሳሳይ የረሃብ አደጋዎችን እንዳይደርሱ ሁሉን አቀፍ ዛላቂ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚጋባም አሳስበዋል ። ክሊንተን እንዳሉት የረሐብ አደጋን ለመከላከል የዓለም ማሕበረሰብ በግብርናና በተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ይገባዋል ። አበበ ፈለቀ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅቷል ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ