1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርጫ ዘመቻ በአሜሪካን

ዓርብ፣ ነሐሴ 13 2008

የዴሞክራቶቹ ፓርቲ እጩ ፕሬዝዳንት ሂለሪ ክሊንተን እና የሪፐብሊካኖቹ እጩ ዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ የአሜሪካን ግዛቶች እየተዘዋወሩ ከተመረጡ እናከናውናለን የሚሏቸውን ለህዝቡ ቃል እየገቡ ነው ።

https://p.dw.com/p/1Jlwa
US Wahlen Hillary Clinton in Iowa
ምስል Reuters/C. Keane

[No title]

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ወደ 80 የሚጠጉ ቀናት ብቻ ናቸው የቀሩት ። ለምርጫው የሚካሄደው የምረጡኝ ዘመቻ ተጧጡፎ ቀጥሏል ። በሁለቱ ተፎካካሪዎች ማለትም የዴሞክራቶቹ ፓርቲ እጩ ሂለሪ ክሊንተን እና የሪፐብሊካኖቹ እጩ ዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ የአሜሪካን ግዛቶች እየተዘዋወሩ ከተመረጡ እናከናውናለን የሚሏቸውን ለህዝቡ ቃል እየገቡ ነው ። ቱጃሩ ትራምፕ በሰሞኑ የምርጫ ዘመቻቸው በአሜሪካን ዘረኝነትን አስቀራለሁ የሕግ የበላይነትም እንዲከበር አደርጋለሁ ብለዋል ። የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል ።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ