1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካን የት/ቤት ሕፃናት ግድያ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 8 2005

ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈዉ ሳምንታ ማለቂያ ዓርብ ዕለት ኒዉታዉን በተባለዉ ከተማ በአንድ ትምህርት ቤት ዉስጥ የ20ዓመት ወጣት ድንገት በፈጃቸዉ ህፃናት እና መምህራን ሀዘን ተዉጣለች።

https://p.dw.com/p/174A0
ምስል dapd

 ሀገሪቱ ምንም እንኳን በተደጋጋሚ ይህን መሰል አደጋ የሚገጥማት መሆኑ ቢታይም ከዘመናት በፊት የፀደቀዉን ህገመንግስት ተገን በማድረግ ከ80 ሚሊዮን በላይ ግለሰቦች በየቤታቸዉ የጦር መሳሪያዎችን ገዝተዉ ማስቀመጣቸዉ ይሰማል። ሶስት መሳሪያ ይዞ ወደትምህርት ቤት በመሄድ ህፃናቱን የገደለዉ ወጣት ኋላ ራሱን ማጥፋቱ ቢነገርም መሳሪያዉን ያገኘዉ ከቤቱ እናቱ ገዝተዉ ያስቀመጡት መሆኑም ተገልጿል። በድርጊቱ የተደናገጠዉ ኅብረተሰብ በሃዘን ከመዋጡ ዉጭ ግን መሳሪያን በየግለሰቡ እጅ እንደመጫወቻ የመያዙ ጉዳይ ይታገድ ብሎ በይፋ አለመናገሩን እዚህ ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በጉዳዩ ላይ ያነጋገርኩት ዋሽንግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ገልጾልናል።

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ