1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካኖች ዛቻ፣ AGOAና ኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ጥቅምት 5 2014

ጦርነቱ ካልቆመ ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ የዕድገት ዕድል (በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ AGOA) ካለችዉ የንግድ ትስስር ኢትዮጵያን እንደምትሰርዛት አስጠንቅቃለች

https://p.dw.com/p/41kKt
AGOA Forum 2009
ምስል picture-alliance/dpa

ኢትዮጵያ ብዙ ጉዳት ይደርስባት ይሆን?

ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉን ጦርነትና የሰብባአዊ መብት ጥሰትን «ለማስቆም» ያለችዉን ጫና እና ዛቻ አጠናክራ ቀጥላለች።ጦርነቱ ካልቆመ ዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃ የዕድገት ዕድል (በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ AGOA) ካለችዉ የንግድ ትስስር ኢትዮጵያን እንደምትሰርዛት አስጠንቅቃለች።ትስስሩ ከሳሐራ በስተደቡብ የሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት ቀረጥ ሳይከፍሉ ሸቆጦቻቸዉን ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እንዲያስገቡ የሚፈቅድ ነዉ።ኢትዮጵያ ከ AGOA አባልነት ከተሰረዘች ብዙ ጉዳት ይደርስባት ይሆን?

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ