1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ምክር ቤት ዉሳኔና ትርጓሜዉ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 16 2014

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት የዉጪ ግንኙነት ኮሚቴ ባፀደቀዉ ዉሳኔ የኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት ዉጊያ እንዲያቆሙ፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩና በጦርነቱ ለተጎዳዉ ሕዝብ የሰብአዊ ርዳታ ይደርስ ዘንድ እንዲፈቅዱ ጠይቋል።

https://p.dw.com/p/42D2S
USA Washington | Nach dem Sturm aufs Kapitol
ምስል Str/dpa/picture alliance

የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ዉሳኔና ትርጓሜዉ

 

የዩናይትድስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት ኢትዮጵያን አስመልክቶ ያሳለፈው ውሳኔ  ስለሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ የተሻለ ግንዛቤ የተንጸባረቀበት መሆኑን አንድ የሕግ ባለሙያ አስታወቁ።የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት የዉጪ ግንኙነት ኮሚቴ ባፀደቀዉ ዉሳኔ የኢትዮጵያ ተፋላሚ ኃይላት ዉጊያ እንዲያቆሙ፣ ሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩና በጦርነቱ ለተጎዳዉ ሕዝብ የሰብአዊ ርዳታ ይደርስ ዘንድ እንዲፈቅዱ ጠይቋል።እዚያዉ አሜሪካ የሚኖሩት ዶክተር ፍፁም አቻምየለህ እንዳሉት ውሳኔዉ  ከዚህ ቀደም ከነበሩት ይልቅ ለኢትዮጵያ ጠቃሚና  የምክር ቤቱ አባላትም የተሻለ ግንዛቤ መያዛቸዉን የሚያመላክት ነው::

ታሪኩ ኃይሉ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ