1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የአሜሪካ ም/ቤት የ HR 128 ረቂቅን አፀደቀ 

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 3 2010

የአሜሪካ ኮንግረስ «ምክር ቤት» በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዓዊ መብት እና የዲሞክራሲ ጉዳዮችን የሚመለከተውን ኤች አር 128 ተብሎ የሚታወቀውን የውሳኔ ሀሳብ ትላንት ለዛሬ አጥብያ አጸደቀ፡፡ የውሳኔ ሀሳቡ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ ግድያዎች እንዲጣሩ፣ የታሰሩ እንዲፈቱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ እና አፋኝ የተባሉ ሕግጋት እንዲሻሩ ይጠይቃል፡፡

https://p.dw.com/p/2vtJs
USA Kapitol in Washington | Abstimmung Haushaltssperre
ምስል picture-alliance/newscom/UPI/P. Marovich

ኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩጥሪ አቅርቧል።

 

ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በገለልተኛ አካላት እንዲጣሩ እና ድርጊቱን ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎችም ለህግ እንዲቀርቡ ጥሪ አቅርቧል፡፡ የውሳኔ ሀሳቡ የመብት ጥሰት ፈጽመዋል የተባሉ ግለሰቦች እና ተቋማት ላይም ማዕቀብ እንዲጣል ይሻል፡፡ የውሳኔ ሀሳቡ እንዳይጸድቅ የኢትዮጵያ መንግስት ግፊት ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ዝርዝሩን የዋሽንግተኑ ወኪላችን ልኮልናል። 
መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ 
ሂሩት መለሰ