1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ሴኔትና ሶርያ

ረቡዕ፣ ነሐሴ 29 2005

ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ እና ከፍተኛ ባለስጣኖቻቸዉ የአሜሪካ ምክር ቤት ለፕሬዝደንቱ ሶርያ ላይ ወታደራዊ ጥቃት የመፈጸም መብት እንዲሰጣቸዉ ጥያቄ ማቅረባቸዉን ቀጥለዋል።

https://p.dw.com/p/19cCi
ምስል Reuters

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር፣ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የጦሩ ሹም ለሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላት ትናንት እና ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ፕሬዝደንት ኦባማ በበኩላቸዉ ዓለም ዓቀፍ ድጋፍ እየጋበዙ ነዉ። ስቶክሆልም ስዊድን ላይ ይህን አስመልክተዉ ባደረጉት ንግግርም ሶርያ ላይ ርምጃ ባይወሰድ የእሳቸዉ ሳይሆን የዓለም ዓቀፉ ኅብረተሰብ ተዓማኒነት አጠያያቂ እንደሚሆን አመልክተዋል።
የዋሽንግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝርዝሩን ልኮልናል

አበበ ፈለቀ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ