1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ስለላ እና የአዉሮጳ ህብረት ቅሪታ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 25 2005

አሜሪካ ሚስጥራዊ መረጃዎችን አሳልፎ በመስጠት ወንጀል የምትፈልገዉ የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅት ሰራተኛ ኤድዋርድ ስኖዉደን በ 21 ሀገራት ተገን እንዲሰጠው ማመልከቱ ተሰምቷል ።

https://p.dw.com/p/190ZV
Protesters in support of Edward Snowden, a contractor at the National Security Agency (NSA), hold a photo of him during a demonstration outside the U.S. Consulate in Hong Kong in this June 13, 2013 file photo. Snowden, left Hong Kong on a flight for Moscow on June 23, 2013 and his final destination may be Ecuador or Iceland, the South China Morning Post said. REUTERS/Bobby Yip/Files (CHINA - Tags: POLITICS CIVIL UNREST)
ምስል Reuters

ስኖዉደን ተገን ከጠየቃቸዉ ሀገራት መካከል ጀርመን አንድዋ ስትሆን ለሩስያ ያቀረበዉን የተገን ጥያቄ ግን አንስቶአል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካን ብሔራዊ የስለላ ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር NSA የአዉሮጳን ህብረትን ሰልሏል መባሉ በህብረቱ ሀገራት ሲወገዝ አሜሪካን ፣ ጀርመንን ጨምሮ ከበርካታ ሀገራት ጋር ባላት ዲፕሎማስያዊ ግንኙነት ላይ ጫና እንደሚያደርግ ተገምቷል ። የመንግስታት እና የተለያዩ ድርጅቶችን ምስጢራዊ ሰነዶች ለህዝብ ይፋ እንደ ሚያደርገዉ እንደ ዊኪሊክስ ድረ-ገጽ ገለጻ፤ አሜሪካ ሚስጥራዊ መረጃዎችን አሳልፎ በመስጠት ወንጀል የምትፈልገዉ የቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅት ሰራተኛ ኤድዋርድ ስኖዉደን በ21 ሀገራት የተገን ጥያቄን አቅርቦአል። ከአገራቱ መካከል ደግሞ ቻይና ፈረንሳይ፤ ጀርመን አየርላንድ፤ ቪንዝዊላ ይገኙበታል። ሩስያና ኖርዌይም ከ30 ዓመቱ ጎልማሳ ኤድዋርድ ስኖዉደን የተገን ጥያቄ እንደቀረበላቸዉም ይፋ አድርገዋል። ነገር ገን ዛሪ ረፋዱ ላይ ይፋ እንደሆነዉ ስኖዉደን፤ የክሪምሊንን ቅድመ ሁኔታ ካጤነ በኋላ ለሩስያ ያቀረበዉን ጥያቄ አንስቶአል። ትንናት ሰኞ የሩስያዉ ፕሪዝደንት ቭላድሚር ፑቲን የስኖደንን የተገን ጥያቄ በማስመልከት ሲናገሩ ስኖዉደን ዩናይትድ ስቴትስን እስካልጎዳ ድረስ በሩስያ መኖር ይችላል ግን አሜሪካዊ ሸሪኮቻችንን የሚጎዳን ስራን ማቆም ይኖርበታል ነበር ያሉት

The National Security Agency, located at Fort Meade, MD September 27, 2001 monitors electronic transmisstions around the world as part of the United States intelligence network. Foto: Greg E. Mathieson +++(c) dpa - Report+++
የአሜሪካን ብሔራዊ የስለላ ድርጅት ቢሮምስል picture-alliance/dpa

«ወደ ሆነ ቦታ መሄድ ከፈለገና የሆነ ሀገር የሚቀበለዉ ከሆነ፤ እሰየዉ ነዉ። እዚህ እኛ ጋር መቆየት ከፈለገ ግን አንድ ቅድመ ሁኔታ አለን ። ይህን ማለቴ አስገራሚ ቢመስልም ፣አሜሪካዉያን ተጓዳኞቻችን የሚጎዳን ስራ ሁሉ ማቆም ይኖርበታል። የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ነኝ ስለሚል ፤ በየትኛዉም ህግ ይህን ስራ መግታት አይቻልም። በዚህም ምክንያት ሌላ የሚቆይበትን ቦታ መፈልግ እና ወደዚያ መሄድ ይኖርበታል፤ ግን ይህ ሁሉ መቼ ሊፈጸም እንደሚችል፤ በእዉነቱ አላዉቅም። ይሄን ባዉቅ ኖሮ አሁኑኑ በነገርኳችሁ ነበር።»

People look the passenger plane, flight SU 150 to Havana, docking to a boarding bridge at the Moscow Sheremetyevo airport on June 24, 2013. US intelligence leaker Edward Snowden was set to fly out of Russia today by flight SU 150 to Havana to seek asylum in Ecuador, as Washington demanded Moscow hand over the fugitive to face espionage charges at home. AFP PHOTO / KIRILL KUDRYAVTSEV (Photo credit should read KIRILL KUDRYAVTSEV/AFP/Getty Images)
ምስል Kirill Kudryavtsev/AFP/Getty Images

በሌላ በኩል የአዉሮጳ ህብረት የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የስለላ ተቋም NSA ህብረቱን ሰልሏል ስለመባሉ ማብራርያ እንዲሰጥ ጠይቋል። NSA ፣ የአዉሮጳ ህብረት ቤሮ ኮንፒዉተር ስልቶችን ሰብሮ በመግባት ከዋሽንግተን እና ከኒዉዮርክ ህብረቱን እንደሚሰልል ይፋ ከሆነ ጀምሮ የህብረቱ ተጠሪዎች እና በህብረቱ የሚገኙ አገራት ፖለቲከኞች ተቀባይነት የሌለዉ ስራ ሲሉ በማዉገዝ ዋሽንግተንን ከዚህ ተግባርዋ እንድትቆጠብ አሳስበዋል። እያንዳንዱን ሰዉ በጥርጣሪ መነጽር ዉስጥ ማየት አይቻልም ያሉት፤ በጀርመን ምክር ቤት የአረንጓዴዎቹ ፓርቲ የህዝብ እንደራሴዎች ተጠሪ ዮርገን ትሪቲን፤ ህብረቱ ከዋሽንግተ ጋር ለድርድር የሚቀመጠዉ በቅድምያ የንግድ ምስጢሮች ከስለላ የተጠበቁ እና ያልተበዘበዙ መሆናቸዉ ከተረጋገጠ ብቻ ነዉ።

«በባንክ ስራ የመረጃ ጉዳይ ልዉውጦች፤ እንዲሁም የተራዘመዉ የበረራ መረጃ ልዉዉጥ ስምምነት ከአዉሮጳ ህብረት አኳያ መቋረጥ ይኖርበታል። የነጻ ንግድ ልዉዉጥ ለድርድር የሚቀርበዉ፤ ግልጽ በሆነ ደንብ የንግድ ሚስጥሩን፤ መጠበቅ ሲቻል ብቻ ነዉ። አሜሪካዉያኑ ልክ ቻይናዉያኑ ላይ ወቀሳ እንዳሰሙት ፤ አሁንም እነሱ የኤኮኖሚ ሄደታችንን እየሰለሉ ነዉ» የአሜሪካን ስለላ ከአዉሮጳዉ ህብረት ሃገራት በተለይ በጀርመን ላይ የተጠናከረ መሆኑ ነዉ ይፋ የሆነዉ። ጀርመን በህብረቱ እና በአገርዋ ላይ ይደረጋል የተባለዉን ስለላ ከወዳጆች በኩል በድብቅ ሚስጢርን ማዳማጥ ተቀባይነት የሌለዉ ስትል አዉግዛለች። ጉዳዩም ሙሉ በሙሉ እንዲጣራ ጠይቃለች። በወዳጅነት ግንኑነት አኳያ ይህ አይነቱ ተግባር የማይታሰብ ነዉ ያሉት የሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ ፖለቲከኛና የመጪው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ ፔር ሽታይንብሩክ፤ ጉዳዩን እንዲያጣሩ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልን ጠይቀዋል።

Russian President Vladimir Putin speaks at the presidential summer residence Kultaranta in Naantali, Finland on June 25, 2013. Putin is in Finland for talks on bilateral and Russia-EU issues. AFP PHOTO / LEHTIKUVA / KIMMO MANTYLA *** FINLAND OUT *** (Photo credit should read KIMMO MANTYLA/AFP/Getty Images)
ፕሪዝደንት ቭላድሚር ፑቲንምስል Kimmo Mantyla/AFP/Getty Images

« የምንኖረዉ ህግ ባለበት ሀገር ነዉ። ስለዚህ እንኔ እንደሚመስለኝ የፊደራል ጀርመን መንግስት ያለበትን ሃላፊነት በመጠቀም ሀገሪቱን መጠበቅ አለበት። ከዚያም በላይ ለዩናይትድ ስቴትስ እና ለብሪታንያ በክብር ጥያቄን ማቅረብ ሳይሆን ከዩኤስ እና ብሪታንያ ጋ ጉዳዩን ለማጣራት በመንግስት ደረጃ ንግግር ይጀምራል ብዪ እጠብቃለሁ»

የአዉሮጳ ህብረትን ቅሪታ የሰሙት እና ሶስት አፍሪቃ አገራትን ጎብኝተዉ ዛሪ ወደ አገራቸዉ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚመለሱት ፕሪዝደንት ባራክ ኦባማ በታንዛንያዉ ጉብኝታቸዉ፤ አገራቸዉ ለአጋሯ አዉሮጳ ህብረት የምትሻዉን መረጃ ሁሉ እንደምታቀብል ነዉ አስታውቀው የተባለው የስለላ ጉዳይም እንደሚጣራ ነዉ የገለጹት

Barack Obama telefoniert im Oval Office picture alliance / Photoshot
ፕሪዝደንት ባራክ ኦባማምስል picture alliance/Photoshot

« በዘገባዉ ስለወጣዉ ጉዳይ በትክክል አላዉቅም። የቀረበውን ወቀሳ እንዲያጣሩ አባላቶቼን የዩናይትድ ስቴትስ ብሄራዊ የስለላ ተቋም NSAን ጠይቄያለሁ፤ መልስ ስናገኛኝ ክሱ ስለምን እንደነሆነ በትክክል፤ ሁሉንም መረጃ ለአጋሮቻችን እንደምናስተላልፍ ማረጋገጥ እወዳለሁ»

የአሜሪካን ብሄራዊ የስለላ ድርጅት NSA የአዉሮጳ ህብረትን የመሰለሉ ዜና ይፋ የሆነዉ ፣ በቀድሞዉ የዩናይትድ ስቴትስ የስለላ ድርጅት ሰራተኛ በኤድዋርድ ስኖደን መሆኑ ተዘግቧል። ስኖዉደን ፤ አሜሪካንን የስለላ መረሃ -ግብር ማጋለጡ ጀርመንን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ከአሜሪካን ጋር ባላቸው ዲፕሎማሲ ግንኙነት ላይ ጫና አድርጓል ።

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ