1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ተጨማሪ የስልጠና ድጋፍ ለአፍሪቃ

ሰኞ፣ መስከረም 24 2008

በዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ አገራቸዉ ለአፍሪቃ የምታደርገዉን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/1Gj1j
USA-Afrika-Gipfel 2014
ምስል DW/S. Broll

[No title]

በሰባኛዉ የተመድ ጉባኤ ጎን ለጎን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት አሜሪካ በተለይ ለዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ኢትዮጵያና ሶማሊያ የምታደርገዉን ወታደራዊ የጦር መሣሪያ ድጋፍና ስልጠና አጠናክራ ትቀጥላለች። በተጨማሪም ጠንካራ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ተቋማት እንዲገነቡና ፍትሃዊ ምርጫ በአህጉሪቱ እንዲካሄድ ዩናይትድ ስቴትስ የበኩሏን አስተዋፅኦ እንደምታደርግ ሚኒስትሯ ተናግረዋል። ከዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ