1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሜሪካ ኤምባሲ መግለጫና ማስተባበያዉ

ዓርብ፣ ነሐሴ 5 2009

አዲስ አበባ ወደ ጂጂጋ የሚያጉዞዉ አዉራ ጎዳና «በፀጥታ አስከባሪዎች ተዘግቷል ፤በአካባቢዉ የተኩስ ልዉዉጥ ተደርጓል» በማለት በአዲስ አበበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ያሠራጨዉን ዘገባ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተባበለ።

https://p.dw.com/p/2i5Uw
Hyänen Äthiopien
ምስል Reuters/T.Negeri

ጂጂጋ፤ የአሜሪካ ማስጠንቀቂያ

 የአሜሪካ ዜጎች ወደ አካባቢዉ እንዳይጓዙ ኤምባሲዉ መክሯል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እንደሚሉት ግን በአካባቢዉ የሶማሌንና የኦሮሚያን መስተዳድሮች ድንበር ለማካለል የተጓዘ ቡድን ሥራዉን ሳይሰራ ከመመለሱ በስተቀር የተፈጠረ ግጭትም፤ ተኩስም የለም። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ የአካባቢዉ ነዋሪዎችም ከወትሮዉ የተለየ ነገር የለም ይላሉ። ዮሐንስን ስቱዱዮ ከመግባቴ በፊት በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ