1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ«አሜን ኢትዮጵያ» ድርጅት ጉባዔ 

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 4 2009

በተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የመሰረቱት አሜን ኢትዮጵያ የተባለው ድርጅት ሰሞኑን በአዲስ አበባ ጉባዔ አካሄደ። ይኸው በኔዘርላንድስ የተቋቋመው ድርጅት በጉባዔው ያጎላው ዋና ነጥብ የመደማመጥ እና የመግባባት ባህልን በማዳበር ለልዩነቶች እና ለግጭቶች መፍትሔ ማስገኘት የሚለውን ነው።

https://p.dw.com/p/2b7XM
NO FLASH Symbolbild Frieden
ምስል picture alliance/Arco Images GmbH

Ber. AA('Amen Ethiopia' über Konfliktmanagement & Friedensförderung) - MP3-Stereo

በጉባዔው የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት የመቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ እና ስለሰላም ጥናት እና ምርምር ያደረጉ ምሁራን ተገኝተዋል። በኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ኤጀንሲ ተመዝግቦ የሚሰራው ይኸው ድርጅት ጉባዔውን ያካሄደው የቀድሞው ፕሬዚደንት የመቶ አለቃ ግርማ ወልደጊዮርጊስ ለሰላም ስብሰባዎች በግቢያቸው ባሰሩት አዳራሽ ነበር። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ