1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአምቦ ተቃዉሞ

ዓርብ፣ ሐምሌ 7 2009

አምቦ ከተማ ዉስጥ አዲስ የተጣለዉን ግምታዊ የግብር ተመን በመቃወም አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች እና ፀጥታ አስከባሪዎች ተጋጭተዉ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ

https://p.dw.com/p/2gZjn
Äthiopien Proteste | Ambo Town
ምስል DW/M. Yonas Bula

(Q&A) Ambo Protest - MP3-Stereo

ምዕራብ ሸዋ አምቦ ከተማ ዉስጥ አዲስ የተጣለዉን ግምታዊ የግብር ተመን በመቃወም አደባባይ የወጡ ነዋሪዎች እና ፀጥታ አስከባሪዎች ተጋጭተዉ በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተነገረ።የአይን ምሥክሮች እንዳሉት የግብሩ ተመን ሕዝቡን ይጎዳል የሚሉ ወገኖች አደባባይ ትናንት ወጥተዉ አራት  የመንግሥትና የድርጅት መኪኖችን አጋይተዋል።የኦሮሚያ መስተዳድር የመንግሥት የኮሙኒኬሽን ጉዳይ  ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋም አምቦ ከተማ ዉስጥ ቃዉሞ እንደነበር አምነዋል።ይሁንና ጉዳት የደረሰባቸዉ መኪኖች ሁለት ብቻ መሆናቸዉን ተቃዉሞዉም ባጭር ጊዜ ዉስጥ በቁጥጥር ሥር መዋሉን አስታዉቀዋል።

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ