1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለጊዜው ተቃውሞዎቹ የሚያመጡት ተጨባጭ ነገር ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም።

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 2 2010

በሳምቱ መገባደጃ በዮርዳኖስ፣ በቱርክ፣ በፓኪስታን እና በማሌዥያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ ወጥተው ዶናልድ ትራምፕ ለኢየሩሳሌም የሰጡትን እውቅና ተቃውመዋል። በሊባኖስ፣ በኢንዶኔዥያ፣ በግብፅ እና በፍልስጤም ግዛቶችም ተመሳሳይ ተቃውሞች ታይተዋል።

https://p.dw.com/p/2pAdW
Jerusalem Entscheidung Proteste weltweit
ምስል Reuters/Beawiharta

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ተቃውሞዎች እየተደረጉ ነው

በሳምቱ መገባደጃ በዮርዳኖስ፣ በቱርክ፣ በፓኪስታን እና በማሌዥያ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደባባይ ወጥተው ዶናልድ ትራምፕ ለኢየሩሳሌም የሰጡትን እውቅና ተቃውመዋል። በሊባኖስ፣ በኢንዶኔዥያ፣ በግብፅ እና በፍልስጤም ግዛቶችም ተመሳሳይ ተቃውሞች ታይተዋል። በሊባኖስ ከአሜሪካ ኤምባሲ ፊት ለፊት ተቃዋሚዎች እና ጸጥታ አስከባሪዎች ተጋጭተዋል።

የፍልስጤምን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡት ተቃዋሚዎች የእስራኤልን ባንዲራ እና የዶናልድ ትራምፕን ምሥል ሲያቃጥሉ ታይተዋል። ለጊዜው ተቃውሞዎቹ የሚያመጡት ተጨባጭ ነገር ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም። የአረቡ ዓለም ምን እያለ ነው? መሪዎቹስ? ሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ነቢዩ ሲራክ እንደሚለው በቀጣናው የሚሰማው ቁጣ ከዚህ በፊት ታይቶ የሚታወቅ አይደለም።

ነቢዩ ሲራክ
እሸቴ በቀለ
አርያም ተክሌ