1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የአረና ተቃውሞ 

ዓርብ፣ የካቲት 8 2011

አረና ትግራይ ለሉዓላዊነት እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ትናንት በሰጠዉ መግለጫ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ሙሉ በሙሉ አለመከብርና የዜጎች መፈናቀል አሳሳቢ መሆኑን አስታወቋልም። ሕዝባዊ ወያኔ ሕርነት ትግራይ የሚቆጣጠረዉ የትግራይ ምክር ቤት የአስተዳደርና ወሰንና የማንነት ጉዳይ ከሚሽን መቋቋሙን ተቃዉሞታል።

https://p.dw.com/p/3DTir
Zusammenarbeit von Arena Tigray & Tigray democratic cooperation
ምስል DW/M. Haileselassie

 የአረና ተቃውሞ 

በቅርቡ ማቋቋሚያ አዋጁ በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀውን የአስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን የትግራዩ ተቃዋሚ ፓርቲ አረና ትግራይ ተቃወመ። አረና ትግራይ ለሉዓላዊነት እና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ትናንት በሰጠዉ መግለጫ በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት ሙሉ በሙሉ አለመከብርና የዜጎች መፈናቀል አሳሳቢ መሆኑን አስታወቋልም።ሕዝባዊ ወያኔ ሕርነት ትግራይ የሚቆጣጠረዉ የትግራይ ምክር ቤት የአስተዳደርና ወሰንና የማንነት ጉዳይ ከሚሽን መቋቋሙን ተቃዉሞታል።ተቃዋሚዉ ፓርቲ አረና ትግራይም አዲሱን ኮሚሽን ኢ-ህገመንግሥታዊ ሲል ተቃውሟል። ኢህአዴግ ብቻውን አገሪቱን ወደ ተረጋጋ ሰላም እና ዴሞክራሲ ሊያሸጋግር አይችልም ያለው አረና ብሔራዊ የአንድነት መንግሥት እንዲመሰረትም ጠይቋል።


ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ


ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ