1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአረንጓዴ ጀግኖች ሽልማት

ረቡዕ፣ መስከረም 19 2003

በአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃና ክብካቤ ሥራ አስተዋፅኦ ላበረከቱ፤ እንዲሁም በሥራቸዉ አርአያነት አካባቢያዊና ማኅበራዊ ግንዛቤ ከመፍጠር ባሻገር ተጨባጭ ለዉጥ አስገኝተዋል የተባሉ ግለሰቦች፤

https://p.dw.com/p/PQ1J
ምስል AP

ድርጅቶች፤ ማኅበረሰቦችና፤ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ብሄራዊ የአረንጓዴ ጀግና ሽልማት አገኙ። ትናንት የተከናወነዉ የአረንጓዴ ሽልማት የአካባቢ ተቆርቋሪዎች መድረክ፤ ከUSAID፤ የኢትዮጵያ ቱሪስት ሥራ ድርጅትና፤ ከሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋ በመተባበር እንዳዘጋጀ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል። ተሸላሚዎች የተዘጋጀላቸዉን ሽልማት ከፕሬዝደንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ ተቀብለዋል።

ታደሰ እንግዳዉ፤ ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ