1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአረፋ አከባበር በአፍሪቃና በሌሎች የዓለም ሃገራት

ዓርብ፣ ሐምሌ 24 2012

አብዛኞቹ የምዕራብ አፍሪቃ ሐገራት ሙስሊሞችም ክፉኛ መቸገራቸዉን አስታዉቀዋል። በየመጠለያ ጣቢያዉ የሚገኘዉ በሚሊዮን የሚቆጠር ሙስሊምም በመደበኛዉ ችግሩ ላይ የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት ጭንቀትን ደብሎ በዓሉን ለመዘከር ተገድዷል።

https://p.dw.com/p/3gFUa
Gabun Moschee
ምስል picture-alliance/AA/O. Ebanga

በተለያዩ ሐገራት ዛሬ ጠዋት የተደረገዉ የኢድ አል አድሐ ስግደት የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን ለመከላከል የተወሰዱና የሚወሰዱ እርምጃዎች ያጠለባት ነዉ።ለወትሮዉ ከባዓሉ ዋዜማ ጀምሮ በሕዝብ የምትጥለቀለዉ የኢራቅ ርዕሠ ከተማ ባግዳድ ለአስር ቀናት በተጣለዉ የመንቀሳቀስ እግዳ ምክንያት ዛሬ «ኦና» ነዉ የዋለችዉ። መሳጂድ በመዘጋታቸዉ አብዛኞቹ የከተማይቱ ነዋሪዎች የኢድ አል አድሐ ሶላትን በየቤታቸዉ ለመስገድ ተገድደዋል።አዲስ አበባም ዛሬ በአደባባይ አልተሰገደም። እዚሕ በዶቼ ቬለዋ ቦን ከተማ ምዕመኑ ለጤና የሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎችን በማድረግና በፈረቃ በመከፋፈል እስከ ማርፈጃዉ ድረስ በየመሳጂዱም፣ በየአደባባዩም ሰግዷል። ኮሶቮና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መሳጂድን ለኢድ ሶላት ዘግተዉ ነዉ የዋሉት። ሊባኖስ ግን ከትናንት ጀምሮ ከፊል ክልከላ ቢጣልም ምዕመኑ የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስፈልጉ ጥንቃቄዎችን እንዲያደርግ ከመገደዱ በስተቀር በየመስጂዱ መስገድ ችሏል። በሙስሊም ሕዝብ ብዛት ከዓለም የመጀመሪያዉን ሥፍራ የያዘችዉ ኢንዶኔዥያም ከፍተኛ የጤና ጥንቃቄ እንዲደረግ ከማዘዝዋ በስተቀር የየመስጂድ ሶላትን አልሰረዘችም። አፍቃኒስታን ዉስጥ ከአንዳድ ከተሞች በስተቀር በአብዛኞቹ አካባቢዎች የተሰገደዉ ለኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት ብዙም ጥንቃቄ ሳይደረግ ነዉ። የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት በአብዛኛዉ ዓለም የጤና ብቻ ሳይሆን የምጣኔ ሐብት ቀዉስም ነዉ ያስከተለዉ። አብዛኞቹ የምዕራብ አፍሪቃ ሐገራት ሙስሊሞችም ክፉኛ መቸገራቸዉን አስታዉቀዋል። በየመጠለያ ጣቢያዉ የሚገኘዉ በሚሊዮን የሚቆጠር ሙስሊምም በመደበኛዉ ችግሩ ላይ የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭት ጭንቀትን ደብሎ በዓሉን ለመዘከር ተገድዷል።


አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ