1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አረፋ በድሬዳዋና በሐረር

ዓርብ፣ ሐምሌ 24 2012

በቅርቡ በአካባቢዎቹ የተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ጥላ ቢያጠላበትም በዓሉ በድሬደዋ እና ሐረር በሰላም መከበሩን ነዋሪዎች እና አመራሮች ገለፁ።1441ኛው አረፋ በዓል በከተሞቹ በተካሄደ የስግደት ስነስርዓት ተከብሯል።

https://p.dw.com/p/3gEyA
Äthiopien Stadt Dire Dawa
ምስል DW/T. Waldyes

የአረፋ አከባበር በድሬዳዋና በሐረር 


በሀገሪቱ እየተስፋፋ ያለው የኮሮና ወረርሽኝ ስጋት እና በቅርቡ በአካባቢዎቹ የተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ጥላ ቢያጠላበትም በዓሉ ሰላማዊ በሆነ መልኩ መከበሩን የድሬደዋ እና ሀረር ነዋሪዎች እና አመራሮች ገለፁ ፡፡ 1441ኛው አረፋ በዓል በከተሞቹ በተካሄደ የስግደት ስነስርዓት ተከብሯል ፡፡በድሬደዋ ለ «DW» አስተያየት የሰጡት አቶ ሱልጣን በዓሉ በኮሮና መስፋፋት ሳቢያ እንደወትሮ በአንድ ቦታ ተሰባስቦ በመስገድ ባይከበርም ጥንቃቄን ተከትሎ በጥሩ ሁኔታ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ በበኩላቸው ህብረተሰቡ በዓሉን በመደጋገፍ እና በመተጋገዝ እንዲሁም በአስተዳደሩ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ፤ የኮሮና ችግር እንዲቀረፍ እና የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ዕቅድ እንዲሳካ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡አቶ አቡበከር ሁሴን የተባሉ የሀረሪ ክልል ነዋሪ ለ«DW» በስልክ በሰጡት አስተያየት በዓሉ የሀይማኖት አባቶች በሰጡት መመርያ መሰረት መከበሩን ገልፀዋል፡፡
በሀረሪ ክልል ነዋሪ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር ረምዚ ሱልጣን በበኩላቸው በዓሉ የኮሮና ስርጭት እና የፀጥታ ችግሩ ጥላ ቢያጠላበትም በሰላም መከበሩን አስረድተዋል፡፡
የአረፋ በዓል በተለይ በድሬደዋ ከዋዜማው ጀምሮ በተለያዩ ርችቶች እና መብራቶች በደመቀ መልኩ እየተከበረ ይገኛል፡፡


መሳይ ተክሉ 


ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ