1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓርብ፣ ኅዳር 9 2009

በትላንትናዉ እለት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ  ለዉጭ ዲፕሎማቶችና አምባሳደሮች ሥለ ሐገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ማብራርያ መስጠታቸዉ ሰጥተዋል።ጠቅላይ ሚንስትሩ ባደረጉት ንግግር አሁን በአገሪቱ አለ ያሉት «ሰላምና መረጋጋት» በዚሁ ከቀጠለ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊነሳ እንደሚችልም ገልጠዋል። 

https://p.dw.com/p/2Suck
Ethiopia State of Emergency Merkel (picture alliance / AP Photo)
ምስል picture-alliance/AP Photo

SoE Could be Lifted: Ethiopia PM - MP3-Stereo

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አስፈላጊ ካደረጉት ሁኔታዎች፤ «የዜጎችን ሰላምና ደንነት ወደ ነበረበት መመለስ፣ ለጎብኚዎችና ለዉጭ ዜጎች ደህንነት አስተማማኝ ጥበቃ ማድረግ፣ ለመሰረተ ልማቶችና ለዉጭ ባለሃብቶች ጥበቃ ማድርግ» እንደነበረ በመንግስት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች የህዝብ ግንኙነት ሐላፊ  አቶ መሃመድ ሰኢድ ለዶይቼ ቬሌ ይናገራሉ።

የሃዋሳ ነዋሪ የሆኑት አቶ አማን በከተማቸዉ ችግር ቢኖርም አዋጁ ሰላምን አስፍነዋል ይላሉ።

ከአዲስ አበባ ያገኘዋቸዉ ግለሰብ አዋጁ የማህበረሰቡን እንቅስቃሴ ላይ ምንም ለዉጥ አላመጣም ይላሉ። ግን በኢኮኖሚና ኢንተርኔት ላይ ጫና ፈጥሯል ባይ ናቸዉ።

በወሎ ዩኒቬርስቲ ተማሪ የሆኑት ግን ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉት  ከሐዋሳና ከአዲስ አበባ አስተያየት ሰጪዎች በተለየ ሁኔታ በከተማቸዉ  ሰለምና ደህንነት እንደሌለ ይናገራሉ።

በምስራቅ ሐረርጌ የቆቦ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ደግሞ ተቃዉሞዉ መቀጠሉን ይናገራሉ።የመንግስት ሠላዮችና ፀጥታ አስከባሪዎች ጨለማን ተገን አድርገዉ  «ዘረፋ» እያካሄዱ መሆናቸዉንና ወጣቶችን በብዙ ቁጥር እየታፈሱ ነዉ ይላሉ። ከምስራቅ ወለጋ ከሆሮ ጉዱሩ ወደ ቆቦ ከተማ ለመምህርነት ሄደዉ እዛ የሚኖሩት በቅርብ ታስሮ መለቀቀቸውን ተናግሮ የሰላምና መረጋጋቱ እጦት ከበፊቱ ይልቅ ብሰዋል ይላሉ።

ምክንያቱንም ስያብራሩ፣ «እዚሕ  ሰላምና መረጋጋት የለም። አሁንም ቢሆን በወታደር ነዉ እየተዳደርን ነዉ።  ያለሁበት ቦታ ቢያንስ ከ400 በላይ ወታደሮች ሰፍረዋል። እነሱም በመነደሮች ተበትኖ ማታ ላይ ቦርሳዎችና ጫማዎች የተከለከለዉን ባንድራ አለዉ በሚል ሰበብ ይወስዳሉ። የኔ ጫማ አሁን፣ በሚገርም ነገር፣ የተከለከለ ባንድራ አለዉ በሚል ሰበብ፣ ባንድራዉ የካናዳ ወይም የሌላ ዉጭ አገር ይመስለኛል፣ ሶስት ቀን ማታ ላይ በቤቴ ተመለልሰዉ ስፈትሹ ነበር።»

አዋጁ ከታወጃ በአንድ ወር ጊዜ ዉስጥ 11, 607 ሰዎች በተለያዩ እስር ቤቶችና ወታደራዊ ካምፖች መታሰራቸዉን የአዋጁ አፈፃፀም አጣር ቦርድ በቅርብ መግለፃቸዉ ይታወሳል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሐመድ