1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም አንድምታ

እሑድ፣ መጋቢት 24 2009

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈዉ መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ,ም ለስድስት ወራት የደነገገዉ አስቸጓይ ጊዜያዊ አዋጅ ሐሙስ ዕለት በምክር ቤቱ ለቀጣይ አራት ወራት እንዲራዘም ተወስኗል። አዋጁ የተደነገገበት የስድስት ወራት ዕድሜ የፊታችን ሐሙስ ነበር የሚያከትመዉ።

https://p.dw.com/p/2aTQr
Ethiopia State of Emergency Merkel (picture alliance / AP Photo)
ምስል picture-alliance/AP Photo

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ

 መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመደንገጉ በሕዝብና በሀገር ላይ ሊደርስ ይችል የነበረዉን አደጋ መቆጣጠር እንዳስቻለዉ፤ አሁንም አንፃራዊ ሰላም ማስፈን እንዳስቻለ ይገልጻል። በተቃራኒዉ የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲዎችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎት፤ የየሰብዓዊ መብቶች እንዲጨፈለቁ ምክንያት ሆኗል፤ ስጋትና ፍርሃትንም በሕዝቡ ላይ እንዲሰፍን አድርጓል ይላሉ። ዶቼ ቬለ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አዎንታዊ እና አሉታዎ ተፅዕኖዎች፤ እንዲሁም የመራዘሙን አንድምታ የቃኘ ዉይይት ለዚህ ሳምንት አካሂዷል።ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ

ልደት አበበ