1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አዋጁ ማሻሻያ 

ረቡዕ፣ መጋቢት 6 2009

የኮማንድ ፖስቱ ሃላፊ እና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ዛሬ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ በኤኮኖሚ አውታሮች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከል ተብሎ የተጣለው ሰዓት እላፊ መነሳቱን ተናግረዋል ።

https://p.dw.com/p/2ZF9K
Karte Äthiopien englisch

Beri AA(Ethiopia relaxes emergency measures) - MP3-Stereo

በኢትዮጵያ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ማሻሻያ መደረጉን  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኮማንድ ፖስት ዛሬ አስታወቀ ። የኮማንድ ፖስቱ ሃላፊ እና የመከላከያ ሚኒስትር አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ዛሬ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን በሰጡት መግለጫ በኤኮኖሚ አውታሮች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶችን ለመከላከል ተብሎ የተጣለው ሰዓት እላፊ መነሳቱን ተናግረዋል ። ከዚህ ሌላ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ በቁጥጥር ስር ማዋል ፣ ብርበራ ማድረግ እና ንብረት መያዝ በተሻሻለው መመሪያ እንዲቀር መደረጉንም ሚኒስትሩ አስታውቃዋል ። ሚኒስትሩ እንደተናገሩት ከተነሱት እገዳዎች ውስጥ በራድዮ በቴሌቪዥን በጽሁፍ በፎቶግራፍ ቲያትር እና ፊልም የሚተላለፉ መልዕክቶች ላይ የተጣለው እገዳ ይገኝበታል ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ። 

 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ኂሩት መለሰ