1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እና የአዉሮጳ ኅብረት

ሰኞ፣ የካቲት 12 2010

የአዉሮጳ ኅብረት በኢትዮጵያ በድጋሚ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተወሰነ ጊዜ የተገደበ እና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ የሚያከብር እንዲሆን አሳሰበ። አዋጁ በሀገሪቱ በተለያዩ አካላት መካከል ሊደረግ ለሚገባው ገንቢ ዉይይት እንቅፋት እንዳይሆንም ጠቁሟል።

https://p.dw.com/p/2swMR
Frankreich Eurokorps-Soldaten hissen die EU-Fahne vor dem Parlament in Straßburg 2014
ምስል Getty Images/AFP/P. Hertzog

አዋጁ በተወሰነ ጊዜ የተገደበ እና መሠረታዊ መብቶችን የሚያከብር እንዲሆን አሳስቧል

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከስልጣን መልቀቅ በሀገሪቱ ፈጥሯል ያለውን አስተማማኝ ያልሆነ ሁኔታ ያመለከተዉ የኅብረቱ መግለጫ፤ የሕዝብን ቅሬታዎችን መሠረት በማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የታቀዱ ማሻሻያዎችን ለማድረግ አዲሱ መንግሥት በሙሉ አቅሙ መሥራት እንደሚኖርበትም አመልክቷል።  ገበያዉ ንጉሤ ከብራስልስ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ