1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅና የአዉሮጳ ሕብረት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 8 2009

ወይዘሮ ፌዴሪካ ሞግሆሪኒ ለኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ለአቶ ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ስልክ ደዉለዉ አዋጁ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ ያሳሰባቸዉ መሆኑን ገልፀዋል።የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ግን መንግሥታቸዉ የደነገገዉ አዋጅ መሠረታዊ መብቶችን አይጥስም ብለዉ መናገራቸዉን ሕብረቱ አስታዉቋል

https://p.dw.com/p/2RO1t
Federica Mogherini in Luxemburg
ምስል DW/B. Riegert

(Beri.Brussel) Äthiopien-EU Menschenrechte - MP3-Stereo

የኢትዮጵያ መንግሥት የደነገገዉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የዴሞክራሲ መርሆችንና የዜጎችን መብት ሊጥስ እንደሚችል የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ አስታወቁ።የዉጪ ግንኙነት ሐላፊ ወይዘሮ ፌዴሪካ ሞግሆሪኒ ለኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ለአቶ ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ስልክ ደዉለዉ አዋጁ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ ያሳሰባቸዉ መሆኑን ገልፀዋል።የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትር ግን መንግሥታቸዉ የደነገገዉ አዋጅ መሠረታዊ መብቶችን አይጥስም ብለዉ መናገራቸዉን ሕብረቱ አስታዉቋል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለስ